Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 23:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ከዚያም በፒስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወደሚገኘው ወደ ጾፊም መስክ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያዎችን ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህም በፈስጋ ተራራ ጫፍ ላይ ወዳለው ወደ ጾፊም ሜዳ ወሰደው፤ እዚያም ሰባት መሠዊያ ሠርቶ በእያንዳንዱ ላይ አንድ ኰርማና አንድ አውራ በግ ሠዋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በሜዳ ወደ ተገ​ነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰ​ደው፤ አዞ​ረ​ውም፤ ሰባ​ትም መሠ​ዊ​ያ​ዎች ሠራ፤ በየ​መ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ አንድ ወይ​ፈን፥ አን​ድም አውራ በግ አሳ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ወደ ጾፊምም ሜዳ ወደ ፈስጋ ተራራ ራስ ላይ ወሰደው፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፥ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን አንድም አውራ በግ አሳረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 23:14
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንዳንድ ሰዎች ኰረጆአቸውን ከፍተው ወርቅ እንደ ልባቸው ይመዛሉ፤ ብሩንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ ጣዖት አድርጎ እንዲሠራላቸውም አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ ከተሠራም በኋላ እየሰገዱ ያመልኩታል።


ይህም ሁሉ ሆኖ በገለዓድ ለጣዖት ይሰግዳሉ፤ ለጣዖት የሚሰግዱት ግን ከንቱ ይሆናሉ፤ በጌልገላ ወይፈኖችን ለመሥዋዕት ያቀርባሉ፤ ነገር ግን መሠዊያዎቻቸው ተሰባብረው በእርሻ መካከል የድንጋይ ክምር ሆነው ይቀራሉ።”


ከባሞትም ተነሥተው በሞአባውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ሸለቆ ተጓዙ፤ ይህም ሸለቆ የሚገኘው ከፒስጋ ተራራ ግርጌ በበረሓው ትይዩ ነው።


ባላቅም በለዓምን “ከእስራኤላውያን ሁሉን ሳይሆን ጥቂቱን ብቻ ወደምታይበት ወደ ሌላ ቦታ ከእኔ ጋር እንሂድ፤ በዚያ ሆነህ እነርሱን ርገምልኝ” አለው።


በለዓምም ባላቅን “አንተ እዚህ በሚቃጠለው መሥዋዕትህ አጠገብ ቁም፤ እኔ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ወደዚያ እሄዳለሁ” አለው።


በለዓምም “በዚህ ቦታም ሰባት መሠዊያዎችን ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎችም አምጣልኝ” አለው።


ይልቅስ ተነሥና ወደ ፒስጋ ተራራ ላይ ውጣ፤ በዚያም ላይ ሆነህ ዐይንህ የቻለውን ያኽል የአገሪቱን ሰሜንና ደቡብ፥ ምሥራቅና ምዕራብ አሻግረህ ተመልከት፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ መሄድ ከቶ አይፈቀድልህም።


ሙሴም ከሞአብ ሜዳዎች ተነሥቶ ወደ ነቦ ተራራ ወጣ፤ ከኢያሪኮም በስተምሥራቅ ወዳለው ወደ ፒስጋ ተራራ ጫፍ ደረሰ፤ ከዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን በሙሉ አሻግሮ እንዲመለከት አደረገው፤ ይኸውም ከገለዓድ ግዛት አንሥቶ በስተ ሰሜን በኩል እስካለው እስከ ዳን ከተማ፥


ይህም ምድር ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ ያለውን ግዛት ሁሉ በማጠቃለል በስተደቡብ እስከ ጨው ባሕር፥ እንዲሁም በስተምሥራቅ እስከ ፒስጋ ተራራ ግርጌ የሚደርስ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች