Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 20:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የእስራኤል ሕዝብም “እኛ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ እኛ ወይም እንስሶቻችን ከውሃችሁ ብንጠጣ እንኳ ዋጋ እንከፍላችኋለን፤ እኛ የምንፈልገው በምድራችሁ አልፈን መሄድ ብቻ ነው” ሲሉ መለሱላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እስራኤላውያንም መልሰው፣ “አውራውን መንገድ ይዘን እንሄዳለን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን የትኛውንም ውሃችሁን ከጠጣን ዋጋውን እንከፍላለን፤ በእግር ዐልፈን መሄድ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አንፈልግም።” አሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የእስራኤልም ልጆች እንዲህ አሉት፦ “በጐዳናው እንሄዳለን፥ እኔም ከብቶቼም ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፥ ሌላም ምንም አናደርግም፤ ብቻ በእግራችን እንለፍ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “በተ​ራ​ራው በኩል እና​ል​ፋ​ለን፤ እኛም ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም ከው​ኃህ ብን​ጠጣ ዋጋ​ውን እን​ከ​ፍ​ላ​ለን፤ ይህ ምንም አይ​ደ​ለም፤ በተ​ራ​ራው እን​ለፍ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የእስራኤልም ልጆች፦ በጐዳናው እንሄዳለን፥ እኔም ከብቶቼም ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፥ ሌላም ምንም አናደርግም፤ ብቻ በእግራችን እንለፍ አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 20:19
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእነርሱ ጋር ቊጥሩ የበዛ ሌላ ድብልቅ ሕዝብ ብዙ የበግ፥ የፍየልና የቀንድ ከብት መንጋ እየነዳ ወጣ።


ለምንበላው ምግብና ለምንጠጣው ውሃ ዋጋ እንከፍላለን፤ እኛ የምንፈልገው በአንተ አገር በኩል ማለፍ እንዲፈቀድልን ብቻ ነው።


የሚያስፈልጋችሁን ምግብና ውሃ በገንዘብ ግዙ።’


ላሞቹም መንገዱን ሳይለቁና ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳያዘነብሉ በቀጥታ ወደ ቤትሼሜሽ በማምራት ጒዞአቸውን ቀጠሉ፤ በሚሄዱበትም ጊዜ እምቧ ይሉ ነበር፤ አምስቱ የፍልስጤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ድረስ በመከተል ሸኙአቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች