Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች፥ “በተ​ራ​ራው በኩል እና​ል​ፋ​ለን፤ እኛም ከብ​ቶ​ቻ​ች​ንም ከው​ኃህ ብን​ጠጣ ዋጋ​ውን እን​ከ​ፍ​ላ​ለን፤ ይህ ምንም አይ​ደ​ለም፤ በተ​ራ​ራው እን​ለፍ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እስራኤላውያንም መልሰው፣ “አውራውን መንገድ ይዘን እንሄዳለን፤ እኛም ሆንን ከብቶቻችን የትኛውንም ውሃችሁን ከጠጣን ዋጋውን እንከፍላለን፤ በእግር ዐልፈን መሄድ ብቻ እንጂ ሌላ ምንም አንፈልግም።” አሏቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የእስራኤልም ልጆች እንዲህ አሉት፦ “በጐዳናው እንሄዳለን፥ እኔም ከብቶቼም ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፥ ሌላም ምንም አናደርግም፤ ብቻ በእግራችን እንለፍ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 የእስራኤል ሕዝብም “እኛ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ እኛ ወይም እንስሶቻችን ከውሃችሁ ብንጠጣ እንኳ ዋጋ እንከፍላችኋለን፤ እኛ የምንፈልገው በምድራችሁ አልፈን መሄድ ብቻ ነው” ሲሉ መለሱላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የእስራኤልም ልጆች፦ በጐዳናው እንሄዳለን፥ እኔም ከብቶቼም ከውኃህ ብንጠጣ ዋጋውን እንከፍላለን፥ ሌላም ምንም አናደርግም፤ ብቻ በእግራችን እንለፍ አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 20:19
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግ​ሞም ሌላ ብዙ ድብ​ልቅ ሕዝብ፥ መን​ጎ​ችና ላሞ​ችም እጅግ ብዙም ከብ​ቶች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወጡ።


የም​በ​ላ​ውን ምግብ በገ​ን​ዘብ ሽጥ​ልኝ፤ የም​ጠ​ጣ​ው​ንም ውኃ በገ​ን​ዘብ ስጠኝ፤ በእ​ግሬ ብቻ ልለፍ፤


ከእ​ነ​ርሱ በገ​ን​ዘብ ምግብ ገዝ​ታ​ችሁ ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ውኃም ደግሞ በገ​ን​ዘብ በመ​ለ​ኪያ ገዝ​ታ​ችሁ ትጠ​ጣ​ላ​ችሁ።


ላሞ​ችም ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ወደ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ አቅ​ን​ተው “እምቧ” እያሉ በጎ​ዳ​ናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ሉም፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆ​ችም እስከ ቤት​ሳ​ሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች