Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 20:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኤዶማውያን ግን “አይሆንም! አናሳልፋችሁም!” አሉ፤ ብርቱ የጦር ሠራዊትም አሰልፈው የእስራኤልን ሕዝብ ሊወጉ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኤዶምም እንደ ገና፣ “በዚህ ማለፍ አትችሉም” የሚል መልስ ሰጣቸው። ከዚያም ኤዶም ብዙና ኀይለኛ የሆነ ሰራዊት አሰልፎ ሊወጋቸው ወጣ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እርሱም፦ “አታልፍም” አለ። ኤዶምያስም በብዙ ሕዝብና በጽኑ እጅ ሊገጥመው ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እር​ሱም፥ “በእኔ በኩል አታ​ል​ፍም” አለ። የኤ​ዶ​ም​ያ​ስም ንጉሥ በብዙ ሠራ​ዊት በጽኑ እጅ ሊገ​ጥ​መው ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እርሱም፦ አታልፍም አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 20:20
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባቱ ስለ መረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም “አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ብሎ አሰበ።


መልእክተኞቹም ወደ ያዕቆብ ተመልሰው መጡና “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንተ ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት።


እኔ ሰላምን እደግፋለሁ፤ ስለ ሰላም በምናገርበት ጊዜ እነርሱ ስለ ጦርነት ያወራሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኤዶም ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ወንድሞቻቸውን እስራኤላውያንን በሰይፍ አሳደዋቸዋል፤ ከያዙአቸውም በኋላ ርኅራኄ አላደረጉላቸውም፤ በእነርሱ ላይ ያላቸው ቊጣ ሊበርድም አልቻለም፤


ኤዶማውያን ግን እንዲህ አሉ፤ “በአገራችን አልፋችሁ እንድትሄዱ አንፈቅድላችሁም! ለመግባት ብትሞክሩ ግን በሰልፍ ወጥተን እንወጋችኋለን።”


ኤዶማውያን እስራኤላውያን በግዛታቸው አልፈው እንዳይሄዱ በመከልከላቸው ምክንያት እስራኤላውያን መንገድ ለውጠው በሌላ በኩል ሄዱ።


ከዚያ በኋላ በምድሩ አልፈው እንዲሄዱ ይፈቅድላቸው ዘንድ ወደ ኤዶም ንጉሥ መልእክተኞች ላኩ፤ ነገር ግን የኤዶም ንጉሥ አልፈቀደላቸውም፤ የሞአብንም ንጉሥ እንዲሁ ጠየቁ፤ እርሱም ቢሆን በምድሩ አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ ስለዚህ እስራኤላውያን በቃዴስ ቈዩ፤


ሲሖን ግን እስራኤላውያን አልፈው እንዲሄዱ አልፈቀደላቸውም፤ እንዲያውም መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ በያሐጽ በመስፈር ከእስራኤል ጋር ተዋጋ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች