Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 1:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከስምዖን ነገድ በየትውልዳቸው በየወገናቸውና በየቤተሰባቸው፥ እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነው ወደ ጦርነት ለመውጣት የሚችል ወንድ ሁሉ በየራሳቸው የተቈጠሩት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከስምዖን ዝርያ፦ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 “የስምዖን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቍጥር፥ አንድ በአንድ የተቈጠሩት፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን ወንድ ሁሉ፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የስ​ም​ዖን ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የስምዖን ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች የተቈጠሩ፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ በየራሳቸው፥ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚወጡት ሁሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 1:22
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደገና ፀነሰችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር እንዳልተወደድኩ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ” ስትል ስሙን ስምዖን አለችው።


ዮሴፍ ከእነርሱ ነጠል ብሎ አለቀሰ፤ እንደገናም ወደ እነርሱ ተመልሶ አነጋገራቸውና ስምዖንን ከመካከላቸው ወስዶ በፊታቸው አሰረው።


የስምዖን ልጆች፦ ይሙኤል፥ ያሚን፥ ኦሃድ፥ ያኪን፥ ጾሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሻኡል ናቸው።


መጠጊያዬ እግዚአብሔር ይመስገን! ለሰልፍ ያሠለጥነኛል፤ ለጦርነትም ያዘጋጀኛል።


ከሮቤል ነገድ የተቈጠሩት አርባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።


ኀምሳ ዘጠኝ ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች