ምሳሌ 23:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፥ ደበደቡኝ፥ አላወቅሁምም። መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እፈልጋለሁ ትላለህ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም35 አንተም፣ “መቱኝ፤ አልተጐዳሁም፤ ደበደቡኝ፤ አልተሰማኝም፤ ታዲያ፣ ሌላ መጠጥ እንዳገኝ፣ መቼ ነው የምነቃው?” ትላለህ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 እንዲሁም “ተደብድቤአለሁ፤ ነገር ግን አልተጐዳሁም፤ ተመትቼአለሁ፤ ሕመሙ ግን አልተሰማኝም፤ መቼ ነው የምነቃው? ሌላ ተጨማሪ መጠጥ የምጠጣው መቼ ይሆን?” ትላለህ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 “መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤ ዘበቱብኝ፥ እኔም አላወቅሁም። ከእኔ ጋር የሚሄዱትን መጥቼ እፈልግ ዘንድ መቼ ጧት ይሆናል?” ትላለህ። ምዕራፉን ተመልከት |