ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ዮዲት 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የእስራኤልም ልጆች ይህን በሰሙ ጊዜ ሁሉም በአንድነት አጠቁአቸው እስከ ቾባ ድረስ እየተከተሉ ገደሉአቸው፤ በጠላቶቻቸው ሰፈር የደረሰው ነገር ተነግሮአቸዋልና በኢየሩሳሌምና በተራራ አገር የሚኖሩ ሁሉ መጡ፤ የገለዓድና የገሊላ ሰዎችም ከደማስቆና ከድንበርዋ ባሻገር በታላቅ እልቂት አጠፏቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የእስራኤልም ልጆች በሰሙ ጊዜ ሁሉም በአንድነት እስከ ኮቤ ድረስ ተከትለው አጠፏቸው፤ በጠላቶቻቸው ሰፈር የሆነውን ነገር ነግረዋቸዋልና ከኢየሩሳሌምና ከአውራጃዋ ሁሉ የመጡ ሰዎች እንደዚሁ አጠፏቸው፤ ከገሊላና ከገለዓድም የመጡ ሰዎች አባረሯቸው፤ ከደማስቆና ከአውራጃዋም እስኪሻገሩ ድረስ ታላቅ ሰልፍ አድርገው አጠፏቸው። ምዕራፉን ተመልከት |