Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ሰው ለመከራ ተወልዶአል የአሞራ ግልገሎች ወደ ላይ እየበረሩ ከፍ እንደሚሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ፍንጣሪው ከእሳቱ ላይ ሽቅብ እንደሚወረወር፣ ሰውም ለመከራ ይወለዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የእሳት ፍንጣሪ ከፍም ላይ ተነሥቶ ወደ ዐየር እንደሚበር፥ እንደዚሁም ሰው ለመከራ ይወለዳል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአ​ሞራ ግል​ገ​ሎች ግን ወደ ላይ እየ​በ​ረሩ ከፍ እን​ዲሉ፥ ሰው እን​ዲሁ ለድ​ካም ተወ​ል​ዶ​አል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የአሞራ ግልገሎች ግን ወደ ላይ እየበረሩ ከፍ እንዲሉ፥ ሰው እንዲሁ ለመከራ ተወልዶአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 5:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፥ በመከራም የተሞላ ነው።


“የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን?


የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው፥ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፥ ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ እኛም እንጠፋለንና።


ነገር ሁሉ ያደክማል፥ ሰው ይናገረው ዘንድ አይችልም፥ ዐይን ከማየት አይጠግብም፥ ጆሮም ከመስማት አይሞላም።


ከፀሐይ በታች በደከመበት ድካም ሁሉና በልቡ መጨነቅ የሰው ልጅ ምን ጥቅም ያገኛል?


ዘመኑ ሁሉ ስቃይ፥ ጥረትም ትካዜ ነው፥ ልቡም በሌሊት አያርፍም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።


ድካምንና ጣርን እንዳይ፥ ዘመኔም በእፍረት እንድታልቅ ለምን ከማኅፀን ወጣሁ?


በሰው ከሚደርሰው ፈተና በቀር ምንም አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ መታገሥ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫ መንገድ ደግሞ ያዘጋጅላችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች