Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፥ ነገሬንም ወደ እግዚአብሔር አቀርብ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ ጕዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ወደ እግዚአብሔር እማጠን ነበር፤ ችግሬን ሁሉ እገልጥለት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እለ​ም​ነው ነበር፥ የሁሉ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እጠ​ራው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እኔ ግን እግዚአብሔርን እለምን ነበር፥ ነገሬንም ወደ እግዚአብሔር አቀርብ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 5:8
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ አንተም ታከብረኛለህ።


“እንግዲህ አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፥ በዚያም መልካምን ታገኛለህ።


መንገድህን ለጌታ አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።


ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥሉ።


በዚህም ምክንያት ይህን መከራ ደግሞ እቀበላለሁ፤ ነገር ግን ያመንኩትን አውቃለሁና አላፍርበትም፤ የሰጠሁትንም አደራ እስከዚያ ቀን ድረስ ለመጠበቅ እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ።


ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥ ስእለትህንም ትሰጣለህ።


ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


እግዚአብሔርን ብትሻ፥ ሁሉንም የሚችለውን አምላክ ብትማጸን፥


እናንተ የምታውቁትን እኔ ደግሞ አውቃለሁ፥ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።


ነገር ግን ሁሉን ለሚችል አምላክ መናገር እፈልጋለሁ፥ ከእግዚአብሔርም ጋር ለመዋቀስ እሻለሁ።


“አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥ በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥


ነገር ግን ኩላሊትንና ልብን የምትመረምር በቅንም የምትፈርድ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ሙግቴን ገልጬልሃለሁና በእነርሱ ላይ የሚሆነውን በቀልህን ልይ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች