Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 31:37 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 ጌታ እንዲህ ይላል፦ በላይ ያለው ሰማይ ቢለካ፥ በታችም ያለው የምድር መሠረት ቢመረመር፥ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ትውልድ በሙሉ እጥላለሁ፥ ይላል ጌታ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በላይ ያሉትን ሰማያትን መለካት፣ በታችም ያሉትን የምድር መሠረቶች መመርመር ከተቻለ፣ በዚያ ጊዜ የእስራኤልን ዘር ሁሉ፣ ስላደረጉት ነገር ሁሉ እጥላቸዋለሁ፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በሠሩት በደል ምክንያት ይጥላቸዋል ማለት የሚቻለው የሰማይ ስፋቱ ተለክቶ፥ የምድርም መሠረቶች ሁሉ ተመርምረው ለመታወቅ ቢችሉ ብቻ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰማይ እጅግ ከፍ ቢል፥ የም​ድ​ርም መሠ​ረት ፈጽሞ ዝቅ ቢል በዚያ ጊዜ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ዘር ሁሉ እን​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ በላይ ቢከነዳ፥ የምድርም መሠረት በታች ቢመረመር፥ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ዘር ሁሉ እጥላለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 31:37
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድርንስ በስፋትዋ አስተውለሃታልን? ሁሉን አውቀህ እንደሆነ ተናገር።


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።


ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?


ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፥ ሰማይንም በስንዝር የለካ፥ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፥ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?


ይህ ለኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፥ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልዘልፍሽም ምያለሁ።


ከያዕቆብም ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤ እኔም የመረጥኳቸው ይወርሷታል፥ አገልጋዬቼም በዚያ ይኖራሉ።


አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።


የሰማይን ሠራዊት መቁጠር የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፥ እንዲሁ የባርያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።”


አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም እንድትሰደድ ያደረግኹባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች