Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዕብራውያን 6:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ዘወትር በርሷ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣና ለሚያርሷትም ፍሬ የምትሰጥ መሬት ከእግዚአብሔር በረከትን ትቀበላለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ ተክል ለተከለባትም ሰው ጥቅም የምትሰጥ መሬት ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ምድ​ርም በእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ር​ደ​ውን ዝናም ከጠ​ጣች፥ ያን​ጊዜ ስለ እርሱ ያረ​ሱ​ላ​ትን መላ​ካም ቡቃያ ታበ​ቅ​ላ​ለች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም በረ​ከ​ትን ታገ​ኛ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ብዙ ጊዜ በእርስዋ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት፥ ለሚያርሱአትም ደግሞ የምትጠቅምን አትክልት የምታበቅል፥ ከእግዚአብሔር በረከትን ታገኛለችና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዕብራውያን 6:7
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርም፦ “ምድር ዘርን የሚሰጥ ሣርንና ቡቃያን በምድር ላይ እንደ ወገኑ ዘሩ ያለበትን ፍሬን የሚያፈራ ዛፍን ታብቅል” አለ፥ እንዲሁም ሆነ።


ወደ እርሱም ቀረበ፥ ሳመውም፥ የልብሱንም ሽታ አሸተተ፥ ባረከውም፥ እንዲህም አለ፦ “የልጄ ሽታ እግዚአብሔር እንደ ባረከው እርሻ ሽታ ነው፥


መሄድስ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፥ መመለስስ፥ ነዶአቸውን ተሸክመው በእልልታ ይመጣሉ።


እርሱ ከጌታ ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ጽድቅን ይቀበላል።


በተጠማ ላይ ውኃን በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈሳለሁ፥


እነርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ስፍራዎች ለበረከት አደርጋቸዋለሁ፥ ዝናቡንም በጊዜው አወርዳለሁ፤ የበረከት ዝናቦችም ይሆናሉ።


ጌታ መጥቶ ጽድቅን እስኪያዘንብላችሁ ድረስ እርሱን የመሻት ዘመን ነውና ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፥ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ሰብስቡ፥ ያልታረሰ መሬታችሁን እረሱ።


እኔ በስድስተኛው ዓመት በረከቴን በእናንተ ላይ አዝዛለሁ፤ ምድሪቱም የሦስት ዓመት ፍሬ ታፈራለች።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አስገቡ፤ የሰማያቶችን መስኮቶች ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


የሚጠይቅ ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ የሚያንኳኳ ይከፈትለታል።


በርትቶ ለሚሠራው ገበሬ የፍሬው የመጀመሪያ ድርሻ ለእርሱ ሊሆን ይገባዋል።


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ! ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። እነሆ ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፥ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች