Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፀአት 26:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከሀያውም ሳንቃዎች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከሥራቸው የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ፤ በእያንዳንዱ ጕጠት ሥር አንድ መቆሚያ ሲሆን፣ ለእያንዳንዱም ወጋግራ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በእነርሱም ሥር አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ሁለቱን ተራዳዎች ለማያያዝ እንዲረዱ እያንዳንዱ ተራዳ ሁለት እግሮች ይኑሩት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ከሃ​ያ​ውም ሳን​ቆች በታች አርባ የብር እግ​ሮ​ችን አድ​ርግ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ። ከሌ​ላ​ውም ሳንቃ በታች ለሁ​ለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከሀያውም ሳንቆች በታች አርባ የብር እግሮችን አድርግ፤ ከእያንዳንዱ ሳንቃ በታች ለሁለት ማጋጠሚያዎች ሁለት እግሮች ይሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፀአት 26:19
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለእያንዳንዱም ሳንቃ አንዱን በአንዱ ላይ የሚያያይዙ ሁለት ማጋጠሚያዎች ይሁኑለት፤ ለማደሪያው ሳንቃዎች ሁሉ እንዲሁ አድርግ።


ለማደሪያውም በደቡብ ወገን ሀያ ሳንቃዎችን አድርግ።


ለማደሪያው ለሁለተኛው ወገን በሰሜን በኩል ሀያ ሳንቃዎች፥


ስምንት ሳንቃዎችና ዐሥራ ስድስት የብር እግሮቻቸው ይሁኑ፥ ከእያንዳንዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግሮች ይሆናሉ።


ለመጋረጃውም አምስት ምሰሶች ከግራር እንጨት አድርግ፤ በወርቅም ለብጣቸው፤ ኩላቦቻቸውም ከወርቅ የተሠሩ ይሁኑ፤ አምስትም እግሮች አድርግላቸው።”


ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ።


መቶው የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶ መክሊት መቶ እግሮች ተሠሩ ይኸውም ለአንድ እግር አንድ መክሊት ማለት ነው።


ሙሴ ማደሪያውን ተከለ፥ እግሮቹን አኖረ፥ ሳንቆቹን አቆመ፥ መወርወሪያዎቹን አደረገባቸው፥ ምሰሶቹንም አቆመ።


እግሮቹ በምዝምዝ ወርቅ ላይ የተመሠረቱ የዕብነ በረድ ምሰሶች ናቸው፥ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ዝግባ ዛፍ ምርጥ ነው።


የሜራሪም ልጆች የሚጠብቁት የማደሪያውን ሳንቆች፥ መቀርቀሪያዎቹንም፥ ምሶሶቹንም፥ እግሮቹንም፥ ዕቃዎቹንም ሁሉ መገልገያውንም ሁሉ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች