ዘፀአት 22:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ባለቤቱ ግን ከእርሱ ጋር ቢኖር አይክፈል፤ አከራይቶት ከሆነም ኪራዩን ብቻ ይክፈል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 “አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ተውሶ ሳለ፣ ባለቤቱ በሌለበት ቢጐዳ ወይም ቢሞት ካሳ መክፈል አለበት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 “አንድ ሰው ከሌላው ሰው እንስሳ በውሰት ወስዶ ባለቤቱ በሌለበት እንስሳው ቢሞት ወይም ቢሰበር በውሰት ለሰጠው ሰው ካሳ ይክፈል፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ሰው ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ወይም ቢነጠቅ ፈጽሞ ይክፈለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱ ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ፈጽሞ ይክፈለው። ምዕራፉን ተመልከት |