ዘፀአት 22:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 አንድ ሰው ከባልንጀራው አንዳች ቢዋስ ባለቤቱም ከእርሱ ጋር ሳይኖር ቢጎዳ፥ ወይም ቢሞት፥ ካሳ ይክፈለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 በዱር አራዊት ተበልቶ ከሆነ፣ ከአውሬ የተረፈውን ማስረጃ አድርጎ በማቅረብ፣ ስለ ተበላው እንስሳ ካሳ እንዲከፍል አይጠየቅም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እንስሳውን አውሬ በልቶት ከሆነ ሰውየው የአውሬውን ትራፊ ለማስረጃ ያቅርብ፤ አውሬ ስለ ገደለውም እንስሳ ካሳ አይክፈል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 በምድረ በዳም አውሬ ቢበላው ውዳቂውን ያሳይ፤ አይክፈልም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ተቧጭሮም ቢገኝ ለምስክር ያምጣው፤ በመቧጨሩም ምክንያት አይክፈል። ምዕራፉን ተመልከት |