Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 9:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 በዚህ አገልግሎት ስለ ተፈተናችሁ፥ በክርስቶስ ወንጌል በማመናችሁ ስለ ታዘዛችሁ፥ እነርሱንና ሁሉንም ስለምትረዱበት ልግስና፥ እግዚአብሔርን ያከብራሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የክርስቶስን ወንጌል ተቀብላችሁ ስለ ታዘዛችሁና ለእነርሱም ሆነ ለሌሎች ስላሳያችሁት ልግስና ሰዎች ተፈትኖ ስላለፈው አገልግሎታችሁ እግዚአብሔርን ያከብራሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ይህ የእናንተ የልግሥና አገልግሎት እናንተ የክርስቶስን ወንጌል ተቀብላችሁ ታማኞች መሆናችሁንና ለእነርሱና ለሌሎችም መለገሣችሁን የሚያረጋግጥ ስለ ሆነ ሁሉም እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ክር​ስ​ቶስ ላስ​ተ​ማ​ራት ትም​ህ​ርት ታዝ​ዛ​ች​ኋ​ልና፥ ሁላ​ች​ሁም ደስ ብሎ​አ​ች​ሁና ተባ​ብ​ራ​ችሁ አወ​ጣ​ጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚች በሃ​ይ​ማ​ኖ​ታ​ችሁ ፈተና ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 በዚህ አገልግሎት ስለ ተፈተናችሁ፥ በክርስቶስ ወንጌል በማመናችሁ ስለሚሆን መታዘዝ እነርሱንና ሁሉንም ስለምትረዱበት ልግስና እግዚአብሔርን ያከብራሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 9:13
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምስጋናን የሚሠዋ ያከብረኛል፥ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ።


መልካም ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ እንግዲህ ብርሃናችሁ በሰው ፊት ይብራ።


ሕዝቡም ይህንን አይተው ፈሩ፤ እንዲህ ያለውንም ሥልጣን ለሰው በመስጠቱ እግዚአብሔርን አከበሩ።


ስለምን “ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ! ትሉኛላችሁ? የምለውን ግን አታደርጉም?


ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ አባቴ ይከበራል።


ይህን በሰሙ ጊዜም ዝም አሉና “እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው፤” እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ።


እነርሱም እንደምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና።


ነገር ግን ሁሉም ለምሥራቹ ቃል አልታዘዙም። ኢሳይያስ “ጌታ ሆይ! የተናገርነውን ማን አመነ?” ብሏልና።


ምክር ከሆነ መምከር፤ መስጠት ከሆነ በልግስና መስጠት፤ ማስተዳደር ከሆነ በትጋት ማስተዳደር፤ ምሕረት ማድረግ ከሆነ በደስታ መማር።


ይህም በይሁዳ ካሉት፥ ከማይታዘዙት እንድድን፥ ለኢየሩሳሌምም ያለኝ አገልግሎቴ በቅዱሳን ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው፥


አሁን ግን ተገለጠ፤ በዘላለማዊው አምላክ ትእዛዝ፥ አሕዛብ ሁሉ ለእምነት እንዲታዘዙ፥ በነቢያት መጻሕፍት እንዲያውቁት ተደርጓል፤


በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ክርክርና ማንኛውም የእብሪት እንቅፋት እናፈርሳለን፤ አእምሮን ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን፤


የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ ወደ ጢሮአዳ በመጣሁ ጊዜ፥ በጌታ በሩ ተከፍቶልኝ ነበር፤


ለቅዱሳን በሚደረገው አገልግሎት እነርሱም ተሳታፊ የመሆንን ጸጋ እንዲያገኙ እኛን አጥብቀው ይለምኑ ነበር፤


እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ታላቅ ጸጋ የተነሣ ስለ እናንተም በሚጸልዩበት ጊዜ ይናፍቁአችኋል።


በእኔም ምክንያት እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር።


መልካሙን የእምነት ውጊያ ተዋጋ፤ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የመሰከርህለትን የዘለዓለምን ሕይወት ያዝ።


ለሁሉ ነገር ሕይወት በሚሰጠው በእግዚአብሔርና በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘንድ መልካሙን መታመን በመሰከረ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት አዝሃለሁ፤


የተስፋን ቃል የሰጠው የታመነ ነውና፥ ተስፋ የሚሰጠንን ምስክርነት ያለመናወጥ በጽናት እንጠብቅ፤


እንዲሁም መልካም ማድረግንና ያላችሁን ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ። እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።


ስለዚህ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ! የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤


እንግዲህ በሰማያት የወጣ ትልቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፥ ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ።


ፍጹም ሆኖ ከተገኘም በኋላ ለሚታዘዙት ሁሉ ለዘለዓለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።


አማትዋም፦ “ዛሬ ከየት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን” አለቻት። እርሷም፦ “ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል” ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማቷ ነገረቻት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች