ልጁ ሣራንም ጠራት፤ እጅዋንም ይዞ ሚስት ልትሆነው ለጦብያ ሰጣት፤ “እነሆ በሙሴ ሥርዐት ውሰዳት፤ ወደ አባትህም ቤት አግባት” ብሎ መረቃቸው።
ቀጥሎም እናቷን ጠራና የሚጽፍበትን ወረቀት እንድትሰጠው ጠየቃት። የሙሴ መጽሐፍ በደነገገው መሠረት ሚስቱ እንድትሆን የጋብቻውን ውል ጽፎ ሰጠው።