ልጄ ለአንተ ትገባለችና፥ አንተም ታገባታለህና።
ራጉኤል ንግግሩን ሰምቶ ወጣቱን እንዲህ አለው፦ “ብላ፥ ጠጣ ዛሬ ማታ ተደሰት፤ ወንድሜ ሆይ ልጄ ሣራን ካንተ በቀር ሌላ ሊያገበት መብት የለውም፤ እኔ እንኳን ልሰጣተ ብፈልግ አንተ የቅርብ ዘመዷ ስልሆንህ ላንተ እንጂ ለሌላ ልሰጣት አልችልም። ነገር ግን ልጄ ሆይ እውነቱን ልንገርህ፥