ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እኔም እውነቱን እነግርሃለሁ፤ ይህችን ልጄን ለሰባት ወንዶች አጋባኋት፤ ወደ እርሷም እንደ ገቡ በሌሊት ይሞታሉ፤ ነገር ግን አንድ ጊዜ ደስ ይበልህ፤” ጦብያም፥ “ነገሩን ለኔ እስክትጨርሱልኝ ድረስ፥ ነገሬንም እስክታጸኑልኝ ድረስ በዚህ ምንም አልቀምስም” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ከዚህ ቀደም ከወገኖቻችን መካከል ከሰባት ሰዎች ጋር አጋብቻት ነበር፤ ሁሉም በመጀመሪያው ቀን ማታ ወደ ክፍሏ ሲገቡ ሞቱ። ለአሁን ግን ልጄ ብላ፥ ጠጣ፥ ጌታ ጸጋውንና ሰላሙን ይሰጥሃል።” ጦብያም “የእኔን ነገር እስክትወስንልኝ ምንም አልበላም፥ አልጠጣም” አለ። ራጉኤልም እንዲህ አለው “መልካም፤ በሙሴ መጽሐፍ መሠረት ለአንተ ተሰጥታለች፥ ለአንተ እንድትሰጥ ሰማይ እራሱ ደንግጓል፥ ስለዚህ እኀትህን ለአንተ ሰጥቻታለሁ፤ ከአሁን ጀምሮ ወንድሟ ነህ፥ እርሷም እኀትህ ናት። ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም ለአንተ ተሰጥለች። ልጄ የሰማዩ ጌታ በዚህች ሌሊት ሞገስ ይሁናችሁ፤ ጸጋውንና ሰላሙን ይስጣችሁ።” ምዕራፉን ተመልከት |