መጽሐፈ ጦቢት 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰባት ወንዶች አጋብተዋት እንደ ወንድና ሴት ሳይቃረቡ አስማንድዮስ የሚባል ክፉ ጋኔን ገድሏቸዋልና፤ እንዲህም አሏት፥ “ባሎችሽ እየታነቁ እንደሚሞቱ አታውቂምን፦ እነሆ ሰባቱ አገቡሽ፤ ከእነርሱም አንዱ ስንኳ አልተከተለሽም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባት ጊዜ በጋብቻ ተሰጥታ ወንድ ከሴት ጋር እንደሚያደርገው ከእርሷ ጋር ከመተኛታቸው በፊት አስሞዴዩስ የተባለ ክፉ ጋኔን ባሎችዋን ይገላቸው ነበርና። ያች አገልጋይ እንዲህ አለቻት “ባሎችሽን የምትገድያቸው አንቺ ነሽ፥ ለሰባት ባሎች ተሰጥተሽ ነበር፥ ግን ከአንዱም ጋር አብረሽ አልኖርሽም፥ |