መጽሐፈ ጦቢት 3:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም በሰማች ጊዜ ለመታነቅ እስከምትመኝ ድረስ እጅግ አዘነች። እንዲህም አለች፥ “እኔ ለአባቴና ለእናቴ አንዲት ነኝ፤ እንደዚህም ባደርግ ተግዳሮት እሆንበታለሁ፤ ሽምግልናውንም፥ ሰውነቱንም በጭንቅ ወደ መቃብር አወርዳታለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያን ቀን አዘነች፥ ምርር ብላ አለቀሰች፥ ራስዋን ለመስቀል ወደ አባቷ ክፍል ገባች፤ ነገር ግን እንዲህ ብላ አሰበች፦ “አባቴን ‘የምትወዳትና ብቸኛዋ ልጅህ ከኀዘንዋ ክብደት የተነሣ እራስዋን ገደለች’ በማለት ይወቅሱታል፥ እኔም የአባቴን ሽምግልና ወደ ሞት የሚያፈጥን ኀዘን ማምጣት የለብኝም፤ ስለ ሆነም ራሴን ከመስቀል ይልቅ ዳግም የስድብ ቃላት ላለመስማት ከምኖር እንዲገድለኝ ጌታን እለምነዋለሁ።” |