ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ያን ቀን አዘነች፥ ምርር ብላ አለቀሰች፥ ራስዋን ለመስቀል ወደ አባቷ ክፍል ገባች፤ ነገር ግን እንዲህ ብላ አሰበች፦ “አባቴን ‘የምትወዳትና ብቸኛዋ ልጅህ ከኀዘንዋ ክብደት የተነሣ እራስዋን ገደለች’ በማለት ይወቅሱታል፥ እኔም የአባቴን ሽምግልና ወደ ሞት የሚያፈጥን ኀዘን ማምጣት የለብኝም፤ ስለ ሆነም ራሴን ከመስቀል ይልቅ ዳግም የስድብ ቃላት ላለመስማት ከምኖር እንዲገድለኝ ጌታን እለምነዋለሁ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ይህንም በሰማች ጊዜ ለመታነቅ እስከምትመኝ ድረስ እጅግ አዘነች። እንዲህም አለች፥ “እኔ ለአባቴና ለእናቴ አንዲት ነኝ፤ እንደዚህም ባደርግ ተግዳሮት እሆንበታለሁ፤ ሽምግልናውንም፥ ሰውነቱንም በጭንቅ ወደ መቃብር አወርዳታለሁ።” ምዕራፉን ተመልከት |