በተመለሰ ጊዜም እንዲህ አለኝ፥ “አባቴ! ከወገኖቻችን የተገደለ አንድ ሰው አገኘሁ፤ ሬሳውም በገበያ ወድቆአል።”
ጦቢያ ከወንድሞቻችን መካከል ድኻ ለመፈለግ ሄደ፤ ግን ተመልሶ መጣና “አባቴ” አለኝ፤ እኔም “ምንድነው ልጄ?” አልሁት፤ እሱም “አባቴ ከወገኖቻችን አንዱ ተገድሎ በገበያ ተጥሎአል፤ በታነቀበት እዛው ወድቋል” አለኝ።