መጽሐፈ ጦቢት 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዕድሞው ላይም ወፎች እንዳሉ አላወቅሁም፤ ፊቴም ተገልጦ ሳለ እነዚያ ወፎች በዐይኔ ላይ የሚያቃጥል ኩስ ጣሉብኝ፤ በዐይኔም ብልዝ ወጣብኝ፤ እኔም ወደ ባለ መድኀኒት ሄድሁ፥ ነገር ግን የጠቀመኝ የለም፤ ብቻዬን ወደ ኤልማድያ እስክሄድ ድረስ አኪአክሮስ ይመግበኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግንቡ ላይ ድንቢጦች መኖራቸውን አላወቅሁም ነበር፤ ትኩስ ኩሳቸውም በዐይኖቼ ላይ ወደቀብኝና ነጭ ነጥብ ሆነ፤ ለመታከም ወደ ሐኪሞች ሄድሁ፥ ግን መድኃኒት ባደረጉልኝ ቍጥር ነጥቦቹ እየተጨመሩ ሄዱና ጭራሹን ታወርሁ። ለአራት ዓመታት ማየት አልቻልሁም፤ ዘመዶቼም በኔ ነገር በጣም ያዝኑ ነበር፤ አሂካር ወደ ኤሊማይስ እስከሄደበት ጊዜ ድረስ ለሁለት ዓመታት ተንከባከበኝ። |