ወደ ሀገሬም በተመለስሁ ጊዜ ሚስቴን ሐናንና ልጄን ጦብያን መለሰልኝ። በሰባተኛው ሱባኤ በተቀደሰችው የበዓለ ኀምሳ ዕለት ለእኔ መልካም ነገር አደረጉልኝ፤ እበላም ዘንድ ተቀመጥሁ።
በንጉሥ ኤሳራዶን ዘመን ወደ ቤቴ ተመለስሁ፥ ሚስቴን ሐናንና ልጄን ጦቢትንም መልሰው አመጡልኝ። የሳምንቶች በዓል በሆነው በጴንጤቆስጤ በዓላችን ቀን መልካም እራት ተዘጋጀልኝ፥ እኔም ለመብላት ተቀመጥሁ፤