ከዚህም በኋላ ጦብያ ሄደ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነው፤ መንገዱን አቅንቶለታልና። ራጉኤልና ሚስቱ አድናም አመሰገኑት፤ እነርሱም ሄዱ፤ ወደ ነነዌም ቀረቡ።
ጦብያ በደስታና በሰላም ከራጉኤል ቤት ወጣ፤ በደስታው የሰማይና የምድር፥ የሁሉም ንጉሥ የሆነውን ጌታ መንገዱን ስላቃናለት አመሰገነ። ራጉኤልንና ሚስቱን ኤድናን እንዲህ ሲል ባረካቸው “በቀሪው ዘመኔ ሁሉ እናንተን እንዳከብር በጌታ ታዝዣለሁ።”