ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እርሱም፥ “ልጆች ሆይ፥ ሳልሞት የሰማይ ጌታ በጎ ነገር ያድርግላችሁ” ብሎ መረቃቸው፤ ልጁንም እንዲህ አላት፥ “አማቶችሽን አክብሪ፤ እንግዲህ ወዲህ ዘመዶችሽ እነርሱ ናቸውና፤ እኛም በአንቺ መልካሙን እንስማ” ብሎ ሳማት። አድናም ጦብያን አለችው፥ “አንተ የምወድህ ወንድሜ ሆይ፥ የሰማይ ጌታ ከልጄ ከሣራ ልጆችን ሰጥቶህ አይልህ ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ደስ ይለኝ ዘንድ ጎዳናህን ያቅናልህ። እነሆ፥ ልጄን አደራ ሰጥቼሃለሁ፤ አታሳዝናት።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ልጁን ሣራንም እንዲህ አላት “አማቾችሽን አክብሪያቸው፥ ምክንያቱም ከእንግዲህ ወዲህ ከወለዱሽ ይልቅ ወላጆች የሚሆኑሽ እነሱ ናቸውና፤ በሰላም ሂጂ ልጄ፥ በሕይወቴ ሳለሁ ስለ አንቺ መልካም ወሬ ብቻ ያሰማኝ።” ተሰናበታቸውና ሸኛቸው። ኤድናም በተራዋ ጦብያን እንዲህ አለችው “እጅግ የተወደድህ ልጄና ወንድሜ፥ ጌታ በደኀና ይመልስህ፥ እኔም ከመሞቴ በፊት ያንተንና የልጄን የሣራን ልጆች ለማየት ያብቃኝ፤ በጌታ ፊት ልጄን እንድትጠብቃት ለአንተ አስረክባታለሁ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ምንጊዜም አታሣዝናት፤ በሰላም ሂዱ ልጄ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እኔ እናትህ ነኝ፥ ሣራ ደግም እኀትህ ናት። ሁላችንም በሕይወት ዘመናችን ሁሉ በደስታ ያኑረን።” ከዚህ በኋላ ሁለቱንም ሳመቻቸውና በደስታ ሸኘቻቸው። ምዕራፉን ተመልከት |