Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽ​ሐፈ ጦቢት 10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የጦ​ብያ ወላ​ጆች እንደ ተጨ​ነቁ

1 አባቱ ጦቢት ግን ቀኑን ይቈ​ጥር ነበር። ቀጠ​ሮ​ውም አልቆ ሳይ​መጡ በቀሩ ጊዜ፥

2 እን​ዲህ አለ፥ “ምና​ል​ባት እነሆ፥ ልጄ ታስሮ ይሆን? ወይስ ገባ​ኤል ሞቶ ብሩን የሚ​ሰ​ጠው አላ​ገኘ ይሆን?”

3 እጅ​ግም አዘነ።

4 ሚስ​ቱም፥ “ልጄስ ሞት​ዋል፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ዘገየ” አለ​ችው።

5 እን​ዲ​ህም እያ​ለች ታለ​ቅስ ጀመ​ረች፤ “ያይ​ኔን ብር​ሃን ልጄን ያጠ​ፋ​ህ​ብኝ ባይ​ሆን ባላ​ሳ​ዘ​ነ​ኝም ነበር።”

6 እር​ሱም፥ “ዝም በዪ፤ አት​ጨ​ነቂ፤ እር​ሱስ ደኅና ነው” አላት።

7 እር​ሷም አለ​ችው፥ “አን​ተም ዝም በል፤ አታ​ታ​ለኝ፤ ልጄስ ሞት​ዋል።” ታለ​ቅ​ስ​ለ​ትም ዘንድ በሄ​ደ​በት ጎዳና ሁል​ጊዜ ትሄድ ነበር። የሰ​ርጉ በዓል ሳያ​ልቅ እን​ዳ​ይ​ሄድ ራጉ​ኤል ያማ​ለው ዐሥራ አራቱ የበ​ዐ​ዓል ቀን እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ለል​ጅዋ ለጦ​ብያ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ች​ለት በቀን እህል አት​በ​ላም ነበር፤ በሌ​ሊ​ትም ዝም አት​ልም ነበር።


የጦ​ብ​ያና ሣራ ወደ ቤታ​ቸው መመ​ለስ

8 ከዚህ በኋላ የሰ​ርጉ በዐል ባለቀ ጊዜ ጦብያ ራጉ​ኤ​ልን አለው፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ወዲያ አሰ​ና​ብ​ተኝ፤ አባ​ቴና እናቴ ተስፋ ቈር​ጠ​ዋ​ልና እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ያዩኝ ዘንድ ተስፋ አያ​ደ​ር​ጉ​ምና፥”

9 አማ​ቱም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀ​መጥ፤ ወሬ​ህን ይነ​ግ​ሩት ዘንድ እኔ ወደ አባ​ትህ እል​ካ​ለሁ” አለው።

10 ጦብ​ያም፥ “አይ​ሆ​ንም፥ ወደ አባቴ እሄድ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ እንጂ” አለው።

11 ራጉ​ኤ​ልም ተነ​ሥቶ ሚስቱ ሣራ​ንና፥ የገ​ን​ዘ​ቡን እኩ​ሌታ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ከብ​ቶ​ች​ንም፥ ብሩ​ንም ሰጠው።

12 እር​ሱም፥ “ልጆች ሆይ፥ ሳል​ሞት የሰ​ማይ ጌታ በጎ ነገር ያድ​ር​ግ​ላ​ችሁ” ብሎ መረ​ቃ​ቸው፤ ልጁ​ንም እን​ዲህ አላት፥ “አማ​ቶ​ች​ሽን አክ​ብሪ፤ እን​ግ​ዲህ ወዲህ ዘመ​ዶ​ችሽ እነ​ርሱ ናቸ​ውና፤ እኛም በአ​ንቺ መል​ካ​ሙን እን​ስማ” ብሎ ሳማት። አድ​ናም ጦብ​ያን አለ​ችው፥ “አንተ የም​ወ​ድህ ወን​ድሜ ሆይ፥ የሰ​ማይ ጌታ ከልጄ ከሣራ ልጆ​ችን ሰጥ​ቶህ አይ​ልህ ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ደስ ይለኝ ዘንድ ጎዳ​ና​ህን ያቅ​ና​ልህ። እነሆ፥ ልጄን አደራ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አታ​ሳ​ዝ​ናት።”

13 ከዚ​ህም በኋላ ጦብያ ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አመ​ሰ​ገ​ነው፤ መን​ገ​ዱን አቅ​ን​ቶ​ለ​ታ​ልና። ራጉ​ኤ​ልና ሚስቱ አድ​ናም አመ​ሰ​ገ​ኑት፤ እነ​ር​ሱም ሄዱ፤ ወደ ነነ​ዌም ቀረቡ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች