አቤቱ ይቅርታህን ዐሰብሁ፥ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የነበረ ሥራህን ዐሰብሁ፤ አንተን ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች፥ ከጠላታቸውም የምታድናቸው ብፁዓን ናቸውና።
ያኔ ጌታ ሆይ፥ ያንተን ምሕረት፥ ከጥንትም ጀምሮ ያደረግኸውን፥ አንተን በትዕግሥት የጠበቁትን እንዴት አንደታደግኻቸው፥ ከጠላቶቻቸውም እጅ እንዴት እንዳዳንኻቸው አስታወስሁ።