ልጄ ሆይ፥ ሥራህ በሃይማኖትህ ይገለጥ፤ እውነተኞች ሰዎችም ይወድዱሃል።
ልጄ ሆይ የምትሠራውን ሁሉ፥ በደግነት አድርገው፤ ከፍተኛ ስጦታዎችን ከሚያበረክት ሰው አብልጦ ትወደዳለህ።