Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ

መጽሐፈ ሲራክ 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ልጆች ለወ​ላ​ጆ​ቻ​ቸው ማድ​ረግ ያለ​ባ​ቸው ግዴታ

1 ልጆች ሆይ፥ እኔን አባ​ታ​ች​ሁን ስሙኝ፥ በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ እን​ዲህ አድ​ርጉ፤

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ​ትን በል​ጆች ላይ አክ​ብ​ሯ​ልና። የእ​ና​ት​ንም ሥል​ጣን በል​ጆ​ችዋ ላይ ከፍ ከፍ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።

3 አባ​ቱን የሚ​ያ​ከ​ብር ልጅ ኀጢ​አቱ ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።

4 እና​ቱ​ንም የሚ​ያ​ከ​ብ​ራት ልጅ ድልብ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ልብ ነው።

5 አባ​ቱን የሚ​ያ​ከ​ብር ልጅ በል​ጆቹ ደስ ይለ​ዋል፤ በሚ​ጸ​ል​ይ​በ​ትም ቀን ፈጣ​ሪው ይሰ​ማ​ዋል።

6 አባ​ቱን የሚ​ያ​ከ​ብር ልጅ ዕድ​ሜው ይረ​ዝ​ም​ለ​ታል።

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ሰማ ልጅ እና​ቱን ያሳ​ር​ፋ​ታል።

8 እንደ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም ለወ​ላጁ ይገ​ዛል።

9 በረ​ከቱ ትደ​ር​ስህ ዘንድ በቃ​ል​ህም በሥ​ራ​ህም አባ​ት​ህን አክ​ብ​ረው።

10 የአ​ባት በረ​ከት የል​ጅን ቤት ያጸ​ና​ልና፥ የእ​ናት ርግ​ማን ግን መሠ​ረ​ትን ይነ​ቅ​ላል።

11 አባ​ት​ህን በማ​ቃ​ለል አት​መካ፤ አባ​ት​ህን ማቃ​ለል ትም​ክ​ሕት አይ​ሆ​ን​ህ​ምና ሰው በአ​ባቱ ክብር ይከ​ብ​ራል፤ የሰ​ውም ውር​ደቱ እና​ቱን በማ​ቃ​ለሉ ነው።

12 ልጄ ሆይ፥ በእ​ር​ጅ​ናው ጊዜ አባ​ት​ህን ርዳው፥ በሕ​ይ​ወ​ቱም ሳለ አታ​ሳ​ዝ​ነው።

13 ቢያ​ረጅ፥ አእ​ም​ሮ​ው​ንም ቢያጣ ለፈ​ቃዱ እሺ በለው፥ እን​ደ​ሚ​ቻ​ል​ህም አክ​ብ​ረው፥ በአ​ረ​ጀም ጊዜ አታ​ስ​ከ​ፋው፥ ዋጋ በመ​ቀ​በል ጊዜ አባ​ት​ህን መር​ዳ​ትህ አይ​ዘ​ነ​ጋ​ብ​ህ​ምና።

14 ስለ ኀጢ​አ​ትም ፋንታ ጽድቅ ትሠ​ራ​ል​ሃ​ለች።

15 በመ​ከ​ራ​ህም ቀን ይታ​ሰ​ብ​ል​ሃል፤ ፀሐይ በረ​ድን እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ል​ጠው ኀጢ​አ​ቶ​ችህ እን​ደ​ዚሁ ይቀ​ል​ጣሉ።

16 አባ​ቱን የሚ​ጥል ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ደ​ሚ​ፀ​ርፍ ነው፤ እና​ቱን የሚ​ያ​ሳ​ዝ​ና​ትም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ረ​ገመ ነው።


ስለ ትሕ​ትና

17 ልጄ ሆይ፥ ሥራህ በሃ​ይ​ማ​ኖ​ትህ ይገ​ለጥ፤ እው​ነ​ተ​ኞች ሰዎ​ችም ይወ​ድ​ዱ​ሃል።

18 እንደ ገና​ን​ነ​ትህ መጠን እን​ደ​ዚሁ ራስ​ህን አዋ​ርድ። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ዋጋ​ህን ታገ​ኛ​ለህ።

19 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራው ታላቅ ነውና፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንና በት​ሑ​ታን ዘንድ ይመ​ሰ​ገ​ናል።

20 የሚ​በ​ረ​ታ​ብ​ህን አት​ፈ​ልግ፤ የማ​ት​ች​ለ​ው​ንም አት​መ​ር​ምር፤

21 ነገር ግን የታ​ዘ​ዝ​ኸ​ውን ዐስብ። በስ​ውር ያለው ግን አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ።

22 አላ​ስ​ፈ​ላጊ ሥራ​ዎ​ችን አት​መ​ራ​መር፤ ከሰ​ዎች ይልቅ ለአ​ንተ እጅግ ተገ​ል​ጦ​ል​ሃ​ልና።

23 ብዙ ሰዎ​ችን መታ​በ​ያ​ቸው አሳ​ታ​ቸው። ብዙ ሰዎ​ች​ንም የል​ቡ​ና​ቸው ትዕ​ቢት ጣላ​ቸው።

24 ጥፋ​ትን የሚ​ወ​ዳት በእ​ርሷ ይሞ​ታል፥ ክፉ ልቡ​ናም በመ​ጨ​ረ​ሻው ይታ​መ​ማል።

25 ክፉ ልቡና በመ​ከራ ይገ​ረ​ፋል፤ ኀጢ​አ​ተኛ ሰውም በኀ​ጢ​አቱ ላይ ኀጢ​አ​ትን ይጨ​ም​ራል።

26 ለት​ዕ​ቢ​ተ​ኞች ጥፋት ፈውስ የላ​ትም፤ ክፉ ተክል በው​ስ​ጣ​ቸው ሥር ሰድ​ዶ​አ​ልና።

27 የብ​ልህ ሰው ልቡና ምሳ​ሌን ይተ​ረ​ጕ​ማል፤ የዐ​ዋቂ ሰው ጆሮም ጥበብ መስ​ማ​ትን ትወ​ዳ​ለች።


ስለ ምጽ​ዋት

28 የም​ት​ነ​ድድ እሳ​ትን ውኃ ያጠ​ፋ​ታል። ምጽ​ዋ​ትም ኀጢ​አ​ትን ታስ​ተ​ሰ​ር​ያ​ለች።

29 ምጽ​ዋ​ትን ለሚ​ሰጥ ሰው በመ​ጨ​ረሻ ይታ​ሰ​ብ​ለ​ታል፤ በሚ​ሰ​ነ​ካ​ከ​ል​በ​ትም ጊዜ መጠ​ጊ​ያን ያገ​ኛል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች