የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ ተነሥ፤ በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ተነ​ሣ​ባ​ቸው፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ባዘ​ዝ​ኸው ሥር​ዐት ተነሥ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሆይ፤ በመዓትህ ተነሥ፤ በቍጣ በተነሡብኝ ላይ ተነሥ፤ አምላኬ ሆይ፤ ንቃ፤ ትእዛዝም አስተላልፍ!

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሆይ! በቊጣህ ተነሥ፤ የጠላቶቼንም ቊጣ አስወግድ፤ ፍርድ እንዲስተካከል ባዘዝከው መሠረት እኔን ለመርዳት ተነሥ፤

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 7:6
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ሴ​ሎ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ “የአ​ር​ካ​ዊው የኩሲ ምክር ከአ​ኪ​ጢ​ፌል ምክር ይሻ​ላል” አሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ቤ​ሴ​ሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​ካ​ሚ​ቱን የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር እን​ዲ​በ​ትን አዘዘ።


ጥል​ቁም እንደ ልብስ ክዳኗ ነው፥ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ውኆች ይቆ​ማሉ።


እኔ ግን በቸ​ር​ነ​ትህ ታመ​ንሁ፥ ልቤም በማ​ዳ​ንህ ደስ ይለ​ዋል።


ከመ​ን​ፈ​ስህ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ከፊ​ት​ህስ ወዴት እሸ​ሻ​ለሁ?


አቤቱ፥ ለእ​ርሱ ትገ​ለ​ጥ​ለት ዘንድ ሰው ምን​ድን ነው? ታስ​በው ዘን​ድስ የሰው ልጅ ምን​ድን ነው?


ተነሥ፥ አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ አድ​ነኝ፤ አንተ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝን ሁሉ መት​ተ​ሃ​ልና፥ የኃ​ጥ​ኣ​ን​ንም ጥርስ ሰብ​ረ​ሃ​ልና።


ኀጢ​አ​ተኛ ራሱን የሚ​ያ​ስ​ት​በ​ትን ነገር ይና​ገ​ራል፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍር​ሀት በዐ​ይ​ኖቹ ፊት የለም።


ወዳ​ጆ​ች​ህም፥ እን​ዲ​ድኑ በቀ​ኝህ አድን፥ ስማ​ኝም።


ወደ ኪዳ​ን​ህም ተመ​ል​ከት፥ የም​ድር የጨ​ለማ ስፍ​ራ​ዎች በኃ​ጥ​ኣን ቤቶች ተሞ​ል​ተ​ዋ​ልና።


ምድ​ርና በእ​ር​ስዋ ውስጥ የሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋን አጸ​ናሁ።


ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ለፍ​ርድ ይነ​ሣል፤ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ሊፈ​ርድ ይነ​ሣል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አሁን እነ​ሣ​ለሁ፤ አሁን እከ​ብ​ራ​ለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላ​ለሁ።


እን​ግ​ዲህ አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድ​ነን።”


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ የክ​ን​ድ​ሽ​ንም ኀይል ልበሺ፤ እንደ ቀድ​ሞ​ውም ዘመን እንደ ጥንቱ ትው​ልድ ተነሺ።