Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 138:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከመ​ን​ፈ​ስህ ወዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ከፊ​ት​ህስ ወዴት እሸ​ሻ​ለሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 በመከራ መካከል ብሄድም፣ አንተ ሕይወቴን ትጠብቃታለህ፤ በጠላቶቼ ቍጣ ላይ እጅህን ትዘረጋለህ፤ በቀኝ እጅህም ታድነኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በመከራ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ሕያው ታደርገኛለህ፥ በጠላቶቼ ቁጣ ላይ እጆቼን ትዘረጋለህ፥ ቀኝህም ታድነኛለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 መከራ ዙሪያዬን በሚከበኝ ጊዜ መከታ ሆነህ በሕይወት ትጠብቀኛለህ፤ በቊጣ የተነሡብኝ ጠላቶቼን ትቃወማቸዋለህ፤ በኀይልህም ትታደገኛለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 138:7
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በፊ​ቱም እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።


ምድ​ርም ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፥ ተና​ወ​ጠ​ችም፥ የተ​ራ​ሮ​ችም መሠ​ረ​ቶች ተነ​ቃ​ነቁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ።


የዘ​ለ​ዓ​ለም በረ​ከ​ትን ሰጥ​ተ​ኸ​ዋ​ልና፥ በፊ​ት​ህም ደስታ ደስ ታሰ​ኘ​ዋ​ለህ።


ኀያል ሆይ፥ በደም ግባ​ት​ህና በው​በ​ትህ፥ ሰይ​ፍ​ህን በወ​ገ​ብህ ታጠቅ።


አቤቱ፥ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ፥ በወ​ገ​ኖ​ችም ዘንድ እዘ​ም​ር​ል​ሃ​ለሁ፤


አም​ላኬ፥ አንተ ጸሎ​ቴን ሰም​ተ​ሃ​ልና፤ ለሚ​ፈ​ሩ​ህም ርስ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ኪዳን አል​ጠ​በ​ቁ​ምና፥ በሕ​ጉም ለመ​ሄድ እንቢ አሉ፤


አቤቱ፥ ጸሎ​ቴን አድ​ምጥ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ስማ።


በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


ስለ​ዚህ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁ​ንም በላ​ያ​ቸው ዘር​ግቶ መት​ቶ​አ​ቸ​ዋል፤ ተራ​ሮ​ችም ተን​ቀ​ጠ​ቀጡ፤ ሬሳ​ቸ​ውም በመ​ን​ገድ መካ​ከል እንደ ጕድፍ ሆኖ​አል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


“መን​ፈስ ከእኔ ይወ​ጣ​ልና፥ የሁ​ሉ​ንም ነፍስ ፈጥ​ሬ​አ​ለ​ሁና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ቀ​ስ​ፋ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊ​ዜም አል​ቈ​ጣ​ች​ሁም።


ጠላ​ቶ​ቹን ሶር​ያ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ሥ​ራቅ፥ አረ​ማ​ው​ያ​ን​ንም ከም​ዕ​ራብ ያን​ቀ​ሳ​ቅ​ስ​በ​ታል፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም በተ​ከ​ፈተ አፍ ይበ​ሉ​ታል። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


ሰው ሁሉ ክፉና በደ​ለኛ ነውና፥ አፍም ሁሉ ዐመ​ፅን ይና​ገ​ራ​ልና፥ ስለ​ዚህ ጌታ በጐ​ል​ማ​ሶ​ቻ​ቸው ደስ አይ​ለ​ውም፤ ለሙት ልጆ​ቻ​ቸ​ውና ለመ​በ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ራ​ራም። በዚህ ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የክ​ን​ዱን ሥጋ ይበ​ላል፤ ምናሴ ኤፍ​ሬ​ምን፥ ኤፍ​ሬ​ምም ምና​ሴን ይበ​ላል፤ እነ​ርሱ በአ​ን​ድ​ነት የይ​ሁዳ ጠላ​ቶች ይሆ​ና​ሉና። በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።


“አንተ ምድ​ርን ሁሉ የም​ታ​ጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ! እነሆ፥ እኔ በአ​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እጄ​ንም እዘ​ረ​ጋ​ብ​ሃ​ለሁ፤ ከድ​ን​ጋ​ዮ​ቹም ላይ አን​ከ​ባ​ል​ል​ሃ​ለሁ፤ የተ​ቃ​ጠ​ለም ተራራ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።


አሁን ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ ከአብ ገን​ዘብ አድ​ርጎ ይህን ዛሬ የም​ታ​ዩ​ት​ንና የም​ት​ሰ​ሙ​ትን አፈ​ሰ​ሰው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች