የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 53:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከፈ​ቃዴ የተ​ነሣ እሠ​ዋ​ል​ሃ​ለሁ፤ አቤቱ፥ መል​ካም ነውና፥ ስም​ህን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምነው ለእስራኤል የሚሆን መዳን ከጽዮን በወጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፣ ያዕቆብ ደስ ይበለው፤ እስራኤልም ሐሤት ያድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያ የሚያስፈራ ሳይኖር እጅጉን ፈሩ፥ እግዚአብሔር የከበቡህን አጥንቶች በትኖአልና፥ እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና አሳፈርሃቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምነው መዳን ለእስራኤል ከጽዮን በመጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፥ የያዕቆብ ልጆች ደስ ይላቸዋል፤ የእስራኤል ሕዝብ ሐሴት ያደርጋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 53:6
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና” እያሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገ​ኑና እያ​ከ​በሩ እርስ በር​ሳ​ቸው ያስ​ተ​ዛ​ዝሉ ነበር፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በተ​መ​ሠ​ረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​ከ​በሩ በታ​ላቅ ድምፅ ዘመሩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በታ​ላቅ ደስታ ደስ አሰ​ኝ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና በዚያ ቀን ትልቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረቡ፤ ደስም አላ​ቸው፤ ሴቶ​ቹና ልጆ​ቹም ደግሞ ደስ አላ​ቸው፤ ደስ​ታ​ቸ​ውም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከሩቅ ተሰማ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢዮ​ብን አዳ​ነው። ኢዮ​ብም ስለ ወዳ​ጆቹ ጸለየ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ተወ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቀድሞ በነ​በ​ረው ገን​ዘቡ ሁሉ ፋንታ ሁለት እጥፍ ከዚ​ያም በላይ አድ​ርጎ ለኢ​ዮብ ሰጠው።


ከበ​ደሌ ፈጽሞ እጠ​በኝ፥ ከኀ​ጢ​አ​ቴም አን​ጻኝ፤


አቤቱ፥ ጆሮ​ህን ወደ እኔ አዘ​ን​ብል ስማ​ኝም፥ ድሃና ምስ​ኪን ነኝና።


አንቺ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።”


የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት ምን ይመ​ል​ሳሉ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን መሠ​ረ​ታት፤ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ሕዝብ አዳ​ና​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የያ​ዕ​ቆ​ብን ድን​ኳን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለማ​ደ​ሪ​ያ​ውም እራ​ራ​ለሁ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም በጕ​ብ​ታዋ ላይ ትሠ​ራ​ለች፤ አዳ​ራ​ሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖ​ሪያ ይሆ​ናል።


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን በመ​ለ​ስሁ ጊዜ በይ​ሁዳ ሀገር በከ​ተ​ሞ​ችዋ፦ የጽ​ድቅ ማደ​ሪያ ሆይ! የቅ​ድ​ስና ተራራ ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይባ​ር​ክህ የሚል ነገ​ርን እንደ ገና ይና​ገ​ራሉ።


“እነ​ሆም በዚያ ወራ​ትና በዚያ ዘመን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ።


ፊቴ​ንም አከ​ብ​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ፊት ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁም ያሸ​ን​ፉ​አ​ች​ኋል። ማንም ሳያ​ሳ​ድ​ዳ​ችሁ ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ።


በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ምድ​ሮች ሳሉ ከእ​ና​ንተ ተለ​ይ​ተው በቀ​ሩት ላይ በል​ባ​ቸው ድን​ጋ​ጤን እሰ​ድ​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በነ​ፋ​ስም የም​ት​ን​ቀ​ሳ​ቀስ የቅ​ጠል ድምፅ ታሸ​ብ​ራ​ቸ​ዋ​ለች፤ ከሰ​ይፍ እን​ደ​ሚ​ሸሹ ይሸ​ሻሉ ፤


የሕ​ዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ የፈ​ረ​ሱ​ት​ንም ከተ​ሞች ሠር​ተው ይቀ​መ​ጡ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወይ​ን​ንም ይተ​ክ​ላሉ፤ የወ​ይን ጠጃ​ቸ​ው​ንም ይጠ​ጣሉ፤ ተክ​ልን ይተ​ክ​ላሉ፤ ፍሬ​ው​ንም ይበ​ላሉ።