የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 27:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ብ​ህን አድን፥ ርስ​ት​ህ​ንም ባርክ፥ ጠብ​ቃ​ቸው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ከፍ ከፍ አድ​ር​ጋ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ፊትህን ከእኔ አትሰውር፤ ተቈጥተህ አገልጋይህን አታርቀው፤ መቼም ረዳቴ ነህና። አዳኝ አምላኬ ሆይ፤ አትጣለኝ፤ አትተወኝም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባርያህ ፈቀቅ አትበል፥ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተወኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አምላኬና አዳኜ ሆይ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ፤ ተቈጥተህም እኔን አገልጋይህን ከአንተ እንድርቅ አታድርገኝ፤ ረዳቴም ስለ ሆንክ ከእኔ አትለይ፤ አትተወኝም።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 27:9
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አን​ተም ልጄ ሰሎ​ሞን ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልብን ሁሉ ይመ​ረ​ም​ራ​ልና፥ የነ​ፍ​ስ​ንም አሳብ ሁሉ ያው​ቃ​ልና የአ​ባ​ቶ​ች​ህን አም​ላክ ዕወቅ፤ በፍ​ጹም ልብና በነ​ፍ​ስህ ፈቃ​ድም ተገ​ዛ​ለት፤ ብት​ፈ​ል​ገው ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ብት​ተ​ወው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይተ​ው​ሃል።


ነፍሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ሰ​ግ​ነ​ዋ​ለች፥ ምስ​ጋ​ና​ው​ንም ሁሉ አት​ረ​ሳም።


ኀጢ​አ​ት​ህን ሁሉ ይቅር የሚ​ል​ልህ፤ ደዌ​ህ​ንም ሁሉ የሚ​ፈ​ው​ስህ፥


ሰነፍ በልቡ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የለም” ይላል። በሥ​ራ​ቸው ረከሱ፥ ጐሰ​ቈ​ሉም፤ በጎ ነገ​ርን የሚ​ሠ​ራት የለም። አን​ድም እንኳ የለም።


እጅ​ህን ከአ​ር​ያም ላክ፥ ከብዙ ውኃም አድ​ነኝ፤ ከባ​ዕድ ልጆ​ችም እጅ፥


በእ​ው​ነ​ትህ ምራኝ፤ አስ​ተ​ም​ረ​ኝም፤ አንተ አም​ላ​ኪ​ዬና መድ​ኀ​ኒቴ ነህና፥ ዘወ​ት​ርም አን​ተን ተስፋ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና።


አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ት​ህን ለዘ​ለ​ዓ​ለም እዘ​ም​ራ​ለሁ። ጽድ​ቅ​ህ​ንም በአፌ ለልጅ ልጅ እና​ገ​ራ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ታ​ች​ሁን የፈ​ታ​ሁ​በት የፍ​ችዋ ደብ​ዳቤ የት አለ? ወይስ እና​ን​ተን የሸ​ጥሁ ከአ​በ​ዳ​ሪ​ዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ተሸ​ጣ​ች​ኋል፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁም እና​ታ​ችሁ ተፈ​ት​ታ​ለች።


ነገር ግን በደ​ላ​ችሁ በእ​ና​ን​ተና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መካ​ከል ለይ​ታ​ለች፤ ይቅ​ርም እን​ዳ​ይ​ላ​ችሁ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ፊቱን ከእ​ና​ንተ ሰው​ሮ​ታል።


ከእ​ነ​ር​ሱም እን​ዳ​ል​መ​ለስ፥ ከእ​ነ​ርሱ ጋር የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምን ቃል ኪዳን እገ​ባ​ለሁ፤ ከእ​ኔም ዘንድ ፈቀቅ እን​ዳ​ይሉ መፈ​ራ​ቴን በል​ባ​ቸው ውስጥ አኖ​ራ​ለሁ።


ገን​ዘብ ሳት​ወዱ ኑሩ፤ ያላ​ች​ሁም ይበ​ቃ​ች​ኋል፤ እርሱ “አል​ጥ​ል​ህም፤ ቸልም አል​ል​ህም” ብሎ​አ​ልና።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ ድን​ጋይ ወስዶ በመ​ሴ​ፋና በአ​ሮ​ጌው ከተማ መካ​ከል አኖ​ረው፤ ስሙ​ንም፥ “እስከ አሁን ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረድ​ቶ​ናል” ሲል “አቤ​ን​ኤ​ዜር” ብሎ ጠራው። እብነ ረድ​ኤት ማለት ነው።