ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።
ጕልበቴ እግዚአብሔር ሆይ፤ እወድድሃለሁ።
ለመዘምራን አለቃ ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ ጌታ ባዳነው ቀን በዚህ መዝሙር ቃል ለጌታ የተናገረው የጌታ ባርያ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ! ኀይል የምትሰጠኝ አንተ ስለ ሆንክ፥ እወድሃለሁ።
እንደ ብልጥግና ሁሉ በምስክርህ መንገድ ደስ አለኝ።
በግፍ የሚጠሉኝ በላዬ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጠሉኝና በዐይናቸው የሚጠቃቀሱብኝም።
በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዐመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤
ዳዊት ግን በዘመኑ ለእግዚአብሔር ትእዛዝ አገልግሎአል፤ እንደ አባቶቹ ሞተ፥ ተቀበረም፤ መፍረስ መበስበስንም አይቶአል።
በሚያስችለኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።
በፍጹም ኀይል፥ በክብሩ ጽናት፥ በፍጹም ትዕግሥት፥ በተስፋና በደስታም ጸንታችሁ።
ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ።
እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።