የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 146:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሃ​ንን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል፥ ኃጥ​አ​ንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፥ እውነትን ለዘለዓለም የሚጠብቅ፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ነው። እርሱ ዘወትር ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 146:6
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመ​ጀ​መ​ሪያ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን ፈጠረ።


ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ውር የሚ​ያ​ማን እር​ሱን አሳ​ደ​ድሁ፤ በዐ​ይኑ ትዕ​ቢ​ተኛ የሆ​ነ​ውና ልቡ የሚ​ሳ​ሳው ከእኔ ጋር አይ​ተ​ባ​በ​ርም።


ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ ሆነ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገን ንገሩ።


ይህ ችግ​ረኛ ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፥ ከመ​ከ​ራ​ውም ሁሉ አዳ​ነው።


ተራ​ሮች ሳይ​ወ​ለዱ፥ ምድ​ርም ዓለ​ምም ሳይ​ሠሩ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።


የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሁሉ አጋ​ን​ንት ናቸ​ውና፤ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር ግን ሰማ​ያ​ትን ፈጠረ።


ሁሉ ታላቅ ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናል፥ ግሩ​ምና ቅዱስ ነውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በስ​ድ​ስት ቀን ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ ፈጥሮ በሰ​ባ​ተ​ኛዋ ቀን ዐር​ፎ​አ​ልና፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ን​በ​ትን ቀን ባር​ኮ​ታል፤ ቀድ​ሶ​ታ​ልም።


“ወዮ! አቤቱ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እነሆ አንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ሳን ምንም ነገር የለም።


ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን የማልህላቸውን እውነት ለያዕቆብ፥ ምሕረትንም ለአብርሃም ታደርጋለህ።


ሁሉም በእ​ርሱ ሆነ፤ ከሆ​ነ​ውም ሁሉ ያለ እርሱ ምንም የሆነ የለም።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ አማ​ል​ክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በኦ​ሪ​ታ​ችሁ ተጽፎ የለ​ምን?


እን​ዲ​ህም አሉ​አ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ? እኛስ እንደ እና​ንተ የም​ን​ሞት ሰዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታ​ችሁ ሰማ​ይና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ያለ​ውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትመ​ለሱ ዘንድ ወን​ጌ​ልን እና​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋ​ለን።


አን​ተም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላክ እንደ ሆነ፥ ለሚ​ወ​ድ​ዱ​ትም፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ ቃል ኪዳ​ኑ​ንና ምሕ​ረ​ቱን እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ የሚ​ጠ​ብቅ የታ​መነ አም​ላክ እንደ ሆነ ዕወቅ፤


በእ​ርሱ ቃል​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሮ​አ​ልና በሰ​ማይ ያለ​ውን፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን፥ የሚ​ታ​የ​ው​ንና የማ​ይ​ታ​የ​ውን፥ መና​ብ​ር​ትም ቢሆኑ፥ አጋ​እ​ዝ​ትም ቢሆኑ፥ መኳ​ን​ን​ትም ቢሆኑ፥ ቀደ​ም​ትም ቢሆኑ፥ ሁሉን በእ​ርሱ ቃል​ነት ፈጥ​ሮ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ለእ​ርሱ ተፈ​ጠረ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።