Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 146:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እርሱም ሰማይንና ምድርን ባሕርንም፥ በእነርሱ ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፥ እውነትን ለዘለዓለም የሚጠብቅ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን፥ ባሕርንና በውስጣቸው ያሉትን ሁሉ የፈጠረ ነው። እርሱ ዘወትር ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዋ​ሃ​ንን ያነ​ሣ​ቸ​ዋል፥ ኃጥ​አ​ንን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 146:6
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ።


ጌታ ቸር፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።


እናንተ ሰማይንና ምድርን በሠራ ጌታ የተባረካችሁ ሁኑ።


ፍቅሩ በእኛ ላይ ጸንቶአልና፥ የጌታም እውነት ለዘለዓለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ።


በጌታ ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ በአፉም እስትንፋስ ሠራዊታቸው ተፈጠረ፥


አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ።


ኃጢአታቸውን በበትር፥ በደላቸውንም በመቅሠፍት እጐበኛታለሁ።


ባሕር የእርሱ ናት እርሱም ፈጠራት፥ የብስንም እጆቹ ሠሩአት።


ለእስራኤል ቤት ያለውን ጽኑ ፍቅርና ታማኝነት አስታወሰ፥ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን አዩ።


ጌታ በስድስት ቀናት ሰማያትንና ምድርን፥ ባሕርን፥ እና በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፤ ስለዚህ ጌታ የሰንበትን ቀን ባርኮታል ቀድሶታልም።


‘አቤቱ ጌታ ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ በእውነት አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ለአንተም ከቶ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም።


ከቀድሞ ዘመን ጀምረህ ለአባቶቻችን እንደማልህላቸው እውነትን ለያዕቆብ፥ ርኅራኄን ለአብርሃም ታደርጋለህ።


ሁሉ በእርሱ ሆነ፤ ከሆነውም ሁሉ አንድም ነገር ያለ እርሱ የሆነ የለም።


ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ፤’ ተብሎ በሕጋችሁ ተጽፎ የለምን?


እንዲህም አሉ “እናንተ ሰዎች! ይህን ስለምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፤ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእርነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።


አንተም ጌታ አምላካችሁ እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ፥ ለሚወዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደሆነ እወቅ፤


የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፤


ከቶውኑ የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት ቃል በገባው የዘለዓለም ሕይወት ተስፋ ያደረገ፤


ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።


በታላቅ ድምፅም “የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውሃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት፤” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች