የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል የሚያቃጥል ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል፤ የሚጋረፍ ነፋስም የእነርሱ ዕድል ፈንታ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 11:6
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሰ​ዶ​ምና በገ​ሞራ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን አዘ​ነበ፤


በፊ​ቱም ከአ​ለው መብል ፈን​ታ​ቸ​ውን አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ የብ​ን​ያ​ምም ፈንታ ከሁሉ አም​ስት እጅ የሚ​በ​ልጥ ነበረ። እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ደስ አላ​ቸው።


በም​ድር ላይ የሸ​ም​ቀቆ ገመዱ ተሰ​ው​ራ​ለች፤ የሚ​ጐ​ት​ተ​ውም በመ​ን​ገዱ ላይ ነው።


በሌ​ሊት በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ለእ​ርሱ የማ​ይ​ሆ​ነው ይኖ​ራል፤ የእ​ር​ሱም መል​ካም ነገር በዲን ይበ​ተ​ናል።


“ሆዱን ቢያ​ጠ​ግብ፥ የመ​ዓት መቅ​ሠ​ፍት ይጨ​መ​ር​በ​ታል፤ የሕ​ማ​ሙም ሥቃይ ይጸ​ና​በ​ታል።


በክ​ር​ክር ውኃ ዘን​ድም አስ​ቈ​ጡት፥ ስለ እነ​ር​ሱም ሙሴ ተበ​ሳጨ፤


ሰኰ​ናዬ እን​ዳ​ይ​ና​ወጥ አረ​ማ​መ​ዴን በመ​ን​ገ​ድህ አጽና።


ከልዩ ሰው ባሪ​ያ​ህን አድ​ነው። ካል​ገ​ዙኝ የዚ​ያን ጊዜ ፍጹም እሆ​ና​ለሁ፥ ከታ​ላ​ቁም ኀጢ​አቴ እነ​ጻ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ምክር ይመ​ል​ሳል፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ዐሳብ ይመ​ል​ሳል። የአ​ለ​ቆ​ችን ምክ​ራ​ቸ​ውን ያስ​ረ​ሳ​ቸ​ዋል።


ፍር​ድን ከሰ​ማይ ታሰ​ማ​ለህ። ምድር ፈራች፥ ዝምም አለች፥


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ የቍ​ጣ​ውን ጽዋ የጠ​ጣሽ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚ​ያ​ን​ገ​ደ​ግ​ድ​ሽን የቍ​ጣ​ውን ጽዋ ጠጥ​ተ​ሻ​ልና፥ ጨል​ጠ​ሽ​ው​ማ​ልና።


ለወ​ገኑ የሚ​ፈ​ርድ አም​ላ​ክሽ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ የሚ​ያ​ን​ገ​ደ​ግ​ድ​ሽን ጽዋ የቍ​ጣ​ዬ​ንም ጽዋ ከእ​ጅሽ ወስ​ጃ​ለሁ፤ ደግ​መ​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አት​ጠ​ጪ​ውም።


ረስ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ታም​ነ​ሻ​ልና ዕጣ​ሽና እድል ፈን​ታሽ ይህ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በመ​ዓቴ በዐ​ውሎ ነፋስ እሰ​ነ​ጣ​ጥ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ያጠ​ፋ​ውም ዘንድ በቍ​ጣዬ የሚ​ያ​ሰ​ጥም ዝናብ፥ በመ​ዓ​ቴም ታላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ር​ዳ​ለሁ።


በቸ​ነ​ፈ​ርና በደም እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ዶፍም፥ የበ​ረ​ዶም ድን​ጋይ፥ እሳ​ትና ድኝም በእ​ር​ሱና በጭ​ፍ​ሮቹ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር በአሉ በብዙ ሕዝብ ላይ አዘ​ን​ባ​ለሁ።


በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፣ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፣ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።


ሎጥ ከሰ​ዶም በወ​ጣ​በት ቀን ግን ከሰ​ማይ እሳ​ትና ዲን ዘነመ፤ ሁሉ​ንም አጠፋ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስን፥ “ሾተ​ል​ህን ወደ አፎቷ መልስ፤ አብ የሰ​ጠ​ኝን ጽዋ ሳል​ጠጣ እተ​ወ​ዋ​ለ​ሁን?” አለው።


ሕል​ቃ​ናም የሚ​ሠ​ዋ​በት ቀን በደ​ረሰ ጊዜ ለሚ​ስቱ ለፍ​ና​ናና ለል​ጆ​ችዋ ሁሉ ዕድል ፋን​ታ​ቸ​ውን ሰጣ​ቸዉ።


ሳሙ​ኤ​ልም ወጥ ቤቱን፥ “በአ​ንተ ዘንድ አኑ​ረው ብዬ የሰ​ጠ​ሁ​ህን እድል ፋንታ አምጣ” አለው።