Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 13:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ረስ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ታም​ነ​ሻ​ልና ዕጣ​ሽና እድል ፈን​ታሽ ይህ ነው፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እኔን ረስተሽ፣ በከንቱ አማልክት ስለ ታመንሽ፣ ያወጅሁልሽ ድርሻሽ፣ ዕጣ ፈንታሽ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ፥ የለካሁልሽም ድርሻሽ ይህ ነው፥ ይላል ጌታ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ዕድል ፈንታችሁም ይህ እንደሚሆን እግዚአብሔር ተናግሮአል። እርሱን ረስታችሁ በሐሰተኞች አማልክት ስለ ታመናችሁ በእናንተ ላይ ይህን ለማድረግ ወስኖአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ረስተሽኛልና፥ በሐሰትም ታምነሻልና ዕጣሽ የለካሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 13:25
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ተኛ ሰው እድል ፋን​ታው፥ ከሚ​ያ​የው ከፈ​ጣ​ሪ​ውም የተ​መ​ደበ ርስቱ ይህ ነው።”


በም​ድር ላይ እንደ ተፈ​ተነ፥ ሰባት ጊዜም እንደ ተጣራ ብር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ንጹሕ ቃል ነው።


ኀጢ​አ​ተ​ኞች ወደ ሲኦል ይመ​ለሱ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ረሱ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ።


“በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ የያ​ዕ​ቆብ ክብር ይደ​ክ​ማል፤ የሚ​በዛ የክ​ብሩ ብል​ጽ​ግ​ናም ይነ​ዋ​ወ​ጣል።


እና​ን​ተም “ከሲ​ኦል ጋር ተማ​ም​ለ​ናል፤ ከሞ​ትም ጋር ቃል ኪዳን አድ​ር​ገ​ናል፤ ሐሰ​ት​ንም መሸ​ሸ​ጊ​ያን አድ​ር​ገ​ና​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም ተሰ​ው​ረ​ና​ልና፥ ዐውሎ ነፋ​ስም ባለፈ ጊዜ አይ​ደ​ር​ስ​ብ​ንም” ትላ​ላ​ች​ሁና፥


እር​ሱም ዕጣ ጣለ​ባ​ቸው፤ እጁም ከፈ​ለ​ች​ላ​ቸው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይሰ​ማ​ሩ​ባ​ታል፤ ከት​ው​ል​ድም እስከ ትው​ልድ ድረስ ይወ​ር​ሱ​አ​ታል፤ በው​ስ​ጥ​ዋም ያር​ፉ​ባ​ታል።


በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ ስላ​ጠኑ፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ስለ አሽ​ሟ​ጠ​ጡኝ ስለ​ዚህ አስ​ቀ​ድ​መው የሠ​ሩ​ትን ሥራ​ቸ​ውን በብ​ብ​ታ​ቸው እሰ​ፍ​ራ​ለሁ።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


ሕዝቤ ግን ረስ​ተ​ው​ኛል፤ ለከ​ንቱ ነገ​ርም አጥ​ነ​ዋል፤ የቀ​ድ​ሞ​ውን ጐዳና ትተው ወደ ጠማ​ማ​ውና ወደ ሰን​ከ​ል​ካ​ላው መን​ገድ ለመ​ሄድ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ተሰ​ና​ከሉ።


ሕዝቤ ሁለት ክፉ ነገ​ሮ​ችን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና፤ የሕ​ይ​ወት ውኃ ምንጭ እኔን ትተ​ው​ኛል፥ የተ​ነ​ደ​ሉ​ትን ውኃ​ው​ንም ይይዙ ዘንድ የማ​ይ​ች​ሉ​ትን ጕድ​ጓ​ዶች ለራ​ሳ​ቸው ቈፍ​ረ​ዋል።


በውኑ ሙሽራ ጌጥ​ዋን ወይስ ድን​ግል ዝር​ግፍ ጌጥ​ዋን ትረ​ሳ​ለ​ችን? ሕዝቤ ግን ለማ​ይ​ቈ​ጠር ወራት ረስ​ቶ​ኛል።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው ዐም​ጸ​ዋ​ልና፥ ቅዱስ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም ረስ​ተ​ዋ​ልና ከብዙ ሰዎች ድምፅ ተሰማ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ልቅ​ሶና ጩኸ​ትም ተሰማ።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ዘን​ግ​ተ​ሽ​ኛ​ልና፥ ወደ ኋላ​ሽም ጥለ​ሽ​ኛ​ልና አንቺ ደግሞ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ተሸ​ከሚ።”


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።


ድምፅን አልሰማችም፥ ተግሣጽንም አልተቀበለችም፣ በእግዚአብሔርም አልታመነችም፥ ወደ አምላክዋም አልቀረበችም።


ከሁለትም ይሰነጥቀዋል፤ እድሉንም ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እው​ነት ሐሰት አድ​ር​ገ​ዋ​ታ​ልና፤ ተዋ​ር​ደ​ውም ፍጥ​ረ​ቱን አም​ል​ከ​ዋ​ልና፤ ሁሉን የፈ​ጠ​ረ​ውን ግን ተዉት፤ እር​ሱም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ ነው፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች