Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ​ዚ​ህም የል​ብ​ስ​ሽን ዘርፍ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ወደ ፊትሽ እገ​ል​ጣ​ለሁ እፍ​ረ​ት​ሽም ይታ​ያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣ ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እግዚአብሔር ራሱ ልብሳችሁን ገፎ ኀፍረተ ሥጋችሁ እንዲጋለጥ ያደርጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 13:26
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኀፍ​ረ​ትሽ ይገ​ለ​ጣል፤ ውር​ደ​ት​ሽም ይታ​ያል፤ ጽድቅ ከአ​ንቺ ይወ​ሰ​ዳል፤ እን​ዲ​ሁም በአ​ንቺ ፋንታ ሰውን አሳ​ልፌ አል​ሰ​ጥም።


በል​ብ​ሽም፦ እን​ዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረ​ሰ​ብኝ? ብትዪ፥ ከኀ​ጢ​አ​ትሽ ብዛት የተ​ነሣ ልብ​ስሽ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ተገ​ፎ​አል፤ ተረ​ከ​ዝ​ሽም ተገ​ል​ጦ​አል።


እኔ ግን ዔሳ​ውን አራ​ቆ​ት​ሁት፤ የተ​ሸ​ሸ​ጉ​ት​ንም ስፍ​ራ​ዎች ገለ​ጥሁ፤ ይሸ​ሸ​ግም ዘንድ አይ​ች​ልም፤ ዘሩም፤ ወን​ድ​ሞ​ቹም፤ ጎረ​ቤ​ቶ​ቹም ጠፍ​ተ​ዋል፥ እር​ሱም የለም።


ሔት። ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እጅግ ኀጢ​አት ሠር​ታ​ለች፤ ስለ​ዚህ ረክ​ሳ​ለች፤ በተ​ጨ​ነ​ቀ​ች​በት ቦታ ያከ​ብ​ሩ​አት የነ​በሩ ሁሉ ውር​ደ​ቷን አይ​ተ​ዋ​ልና አቃ​ለ​ሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም እየ​ጮ​ኸች ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ ወደ ኋላ​ዋም ዘወር አለች።


ስለ​ዚህ እነሆ እኔ ከአ​ንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽ​ሞ​ች​ሽን በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ት​ወ​ጃ​ቸ​ው​ንም ከም​ት​ጠ​ያ​ቸው ጋር በአ​ንቺ ላይ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ይከ​ቡ​ሻል፤ በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ጕስ​ቍ​ል​ና​ሽን እገ​ል​ጥ​ብ​ሻ​ለሁ፤ ሁሉም ኀፍ​ረ​ት​ሽን ያዩ​ብ​ሻል።


እነ​ር​ሱም በጥል ያደ​ር​ጉ​ብ​ሻል፤ የደ​ከ​ም​ሽ​በ​ት​ንም ሁሉ ይወ​ስ​ዳሉ፤ ዕራ​ቁ​ት​ሽ​ንና ዕር​ቃ​ን​ሽን አድ​ር​ገ​ውም ይተ​ዉ​ሻል፤ የግ​ል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ነውር፥ ሴሰ​ኝ​ነ​ት​ሽ​ንና ግል​ሙ​ት​ና​ሽ​ንም ሁሉ ይገ​ል​ጣሉ።


አሁ​ንም በወ​ዳ​ጆ​ችዋ ፊት ነው​ር​ዋን እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ጄም ማንም አያ​ድ​ና​ትም።


እር​ስ​ዋም፥ “ወዳ​ጆች የሰ​ጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለ​ች​ውን ሁሉ ወይ​ን​ዋ​ንና በለ​ስ​ዋን አጠ​ፋ​ለሁ፤ ምስ​ክ​ርም ይሆኑ ዘንድ አኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊ​ትና የሰ​ማይ ወፎች፥ የም​ድር ተን​ቀ​ሳ​ቃ​ሾ​ችም ይበ​ሉ​ታል።


እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ እገልጣለሁ፣ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች