የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የቀዓታውያን ሥራ ንዋየ ቅድሳቱን መጠበቅ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመገናኛው ድንኳን በንዋየ ቅድሳቱ ዘንድ የቀዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእነርሱም አገልግሎት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚገኙትን ንዋያተ ቅድሳት መንከባከብ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በመገናኛው ድንኳን በንዋየ ቅድሳቱ ዘንድ የቀዓት ልጆች ሥራ ይህ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 4:4
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድ​ሶ​ንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራ​ሪም በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው መደ​ባ​ቸው።


የቀ​ዓ​ትም ልጆች ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን ተሸ​ክ​መው ተጓዙ፤ እነ​ዚ​ህም እስ​ኪ​መጡ ድረስ እነ​ዚያ ድን​ኳ​ኑን ተከሉ።


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


ነገር ግን ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ በቀ​ረቡ ጊዜ በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እን​ዲሁ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ አሮ​ንና ልጆቹ ይግቡ፤


የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች ሥራ በማ​ገ​ል​ገ​ልና በመ​ሸ​ከም ይህ ነው፤


ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።


ሰፈሩ በተ​ነሣ ጊዜ አሮ​ንና ልጆቹ ገብ​ተው የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን መጋ​ረጃ ያወ​ር​ዳሉ፤ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት ይጠ​ቀ​ል​ሉ​በ​ታል፤


ለቀ​ዓት ልጆች ግን መቅ​ደ​ሱን ማገ​ል​ገል የእ​ነ​ርሱ ነውና፥ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ይሸ​ከ​ሙት ነበ​ርና ምንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።


ቤቱን ትቶ ወደ ሌላ አገር እንደ ሄደ ሰው ነው፤ ለባሮቹም ሥልጣን ለእያንዳንዱም ሥራውን ሰጥቶ በረኛውን እንዲተጋ አዘዘ።