Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 7:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ለቀ​ዓት ልጆች ግን መቅ​ደ​ሱን ማገ​ል​ገል የእ​ነ​ርሱ ነውና፥ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ይሸ​ከ​ሙት ነበ​ርና ምንም አል​ሰ​ጣ​ቸ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በኀላፊነት የተሰጧቸውን ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው መሸከም ስለ ነበረባቸው፣ ሙሴ ለቀዓታውያን ምንም አልሰጣቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ለቀዓት ልጆች ግን በትከሻቸው በመሸከም ቅዱስ የሆኑትን ነገረሮች ማገልገል የእነርሱ ነበርና፥ ለእነርሱ ምንም አልሰጣቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በእነርሱ ኀላፊነት የሚጠበቁት ንዋያተ ቅድሳት በትከሻቸው የሚሸከሙአቸው ስለ ሆኑ ሙሴ ለቀዓታውያን ሠረገሎችንም ሆነ በሬዎችን አልሰጣቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ለቀዓት ልጆች ግን መቅደሱን ማገልገል የእነርሱ ነውና፥ በትከሻቸውም ይሸከሙት ነበርና ምንም አልሰጣቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 7:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ሰባት መሰ​ንቆ የሚ​መቱ ክፍ​ሎች ነበሩ። በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ችን ይሠዉ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ታቦት በአ​ዲስ ሰረ​ገላ ላይ ጫኑ​አት፥ በኮ​ረ​ብ​ታ​ውም ላይ ከነ​በ​ረው ከአ​ሚ​ና​ዳብ ቤት አመ​ጡ​አት፤ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጆ​ችም ዖዛና ወን​ድ​ሞቹ ታቦቷ ያለ​ች​በ​ትን ሰረ​ገላ ይነዱ ነበር።


ወደ ናኮ​ንም አው​ድማ ደረሱ፤ ዖዛም በሬ​ዎቹ አነ​ቃ​ን​ቀ​ዋት ነበ​ርና ይይ​ዛት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት እጁን ዘረጋ፤ አስ​ተ​ካ​ከ​ላ​ትም። ሲይ​ዛ​ትም በሬው ወጋው።


ካህ​ና​ቱም ታቦ​ቷን አነሡ፤


በቀ​ድሞ ሥራ​ችን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ንም፤ በጦ​ር አል​ፈ​ለ​ገ​ን​ምና” አላ​ቸው።


ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።


ሌዋ​ው​ያ​ንም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ማደ​ሪ​ያ​ው​ንና የማ​ገ​ል​ገያ ዕቃ​ውን ሁሉ አይ​ሽ​ከ​ሙም።”


ታቦ​ቱ​ንም፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብ​ቃሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች