የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 34:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳር​ቻ​ች​ሁም በአ​ቅ​ራ​ቦን ዐቀ​በት በአ​ዜብ በኩል ይዞ​ራል፤ እስከ ኤና​ቅም ይደ​ር​ሳል፤ መው​ጫ​ውም በቃ​ዴስ በርኔ በአ​ዜብ በኩል ይሆ​ናል፤ ወደ አራድ ሀገ​ሮ​ችም ይደ​ር​ሳል፤ ወደ አሴ​ሞ​ናም ያል​ፋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በአቅረቢም መተላለፊያ አቋርጦ እስከ ጺን ይሄድና በስተ ደቡብ እስከ ቃዴስ በርኔ ይዘልቃል፤ ከዚያም በሐጸር አዳር ዐልፎ እስከ ዓጽሞን ይደርስና

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ድንበራችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ይሻገራል፤ በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ያለው መጨረሻው ይሆናል፤ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም ወደ ዐቅራቢም መተላለፊያ ወደ ደቡብ በማምራት በጺን አልፎ እስከ ቃዴስ በርኔ ይደርሳል፤ ከዚያም በሐጻርአዳር ሰሜናዊ ምዕራብ አልፎ እስከ ዓጽሞን ይደርሳል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳርቻችሁም በአቅረቢም ዐቀበት በደቡብ በኩል ይዞራል ወደ ጺንም ያልፋል፤ መውጫውም በቃዴስ በርኔ በደቡብ በኩል ይሆናል፤ ወደ ሐጸርአዳር ይሄዳል ወደ ዓጽሞንም ያልፋል፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 34:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።


ገሥ​ግ​ሠ​ውም በቃ​ዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳ​ሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬ​ው​ንም ለእ​ነ​ር​ሱና ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ፍሬ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም።


ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ክ​ኋ​ቸው ጊዜ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን?


የአ​ዜቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ዶ​ም​ያስ መያ​ያዣ ይሆ​ናል፤ የአ​ዜ​ብም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በም​ሥ​ራቅ በኩል ይጀ​ም​ራል፤


የይ​ሁ​ዳም ነገድ ድን​በር በየ​ወ​ገ​ና​ቸው ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዳርቻ፥ ከጺን ምድረ በዳ ጀምሮ በዐ​ዜብ በኩል እስከ ቃዴስ ድረስ ነው።


የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንም ድን​በር ከአ​ቅ​ራ​ቢም ዐቀ​በት ከጭ​ን​ጫው ጀምሮ እስከ ላይ​ኛው ድረስ ነበረ።