Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 34:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የአ​ዜቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ዶ​ም​ያስ መያ​ያዣ ይሆ​ናል፤ የአ​ዜ​ብም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በም​ሥ​ራቅ በኩል ይጀ​ም​ራል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “ ‘የደቡብ ድንበራችሁ በኤዶም ወሰን ላይ ካለው ከጺን ምድረ በዳ ጥቂቱን ይጨምራል፤ በምሥራቅም በኩል የደቡብ ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ጫፍ ይጀምርና

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምያስን ዳርቻ እያዋሰነ የሚያልፈው ይሆናል፤ የደቡቡም ድንበራችሁ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የደቡብ ድንበር ከጺን ምድረ በዳ ተነሥቶ የኤዶምን ጠረፍ እያዋሰነ ያልፋል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ በኩል የሚጀምረው ከሙት ባሕር በስተ ደቡብ ጫፍ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ይህች ናት፤ የደቡቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤዶምያስ በኩል ይሆናል፤ የደቡቡም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በምሥራቅ በኩል ይጀምራል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 34:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ዚህ ሁሉ በኤ​ሌ​ቄን ሸለቆ ተሰ​ብ​ስ​በው ተባ​በሩ፤ ይኸ​ውም የጨው ባሕር ነው።


ድን​በ​ር​ህ​ንም ከኤ​ር​ትራ ባሕር እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ባሕር፥ ከም​ድረ በዳም እስከ ታላቁ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ አሰ​ፋ​ለሁ፤ በም​ድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን በእ​ጅህ እጥ​ላ​ለ​ሁና፤ ከአ​ን​ተም አስ​ወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ርስት አድ​ር​ጋ​ችሁ ለዐ​ሥራ ሁለቱ የእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ዶች ምድ​ሪ​ቱን የም​ት​ከ​ፍ​ሉ​በት ድን​በር ይህ ነው። ለዮ​ሴፍ ሁለት ዕጣ ይሆ​ናል።


እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ይህ ውኃ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ ገሊላ ይወ​ጣል፤ ወደ ዓረ​ባም ይወ​ር​ዳል፤ ወደ ባሕ​ሩም ይገ​ባል፤ ወደ ባሕ​ሩም ወደ ረከ​ሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃ​ውን ይፈ​ው​ሰ​ዋል።


ወጡም፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ማት ዳር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ ረአብ ድረስ ሰለሉ።


ከሊ​ባ​ኖስ ፊት ለፊት ምድረ በዳ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ድረስ የኬ​ጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሁሉ እስከ ፀሐይ መግ​ቢያ እስከ ታላቁ ባሕር ድረስ ወሰ​ና​ችሁ ይሆ​ናል።


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች