Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ገሥ​ግ​ሠ​ውም በቃ​ዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳ​ሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬ​ው​ንም ለእ​ነ​ር​ሱና ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ፍሬ አሳ​ዩ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሰዎቹም፣ ሙሴና አሮን መላውም የእስራኤላውያን ማኅበረ ሰብ ወዳሉበት በፋራን ምድረ በዳ ወደምትገኘው ወደ ቃዴስ ተመለሱ፤ ያዩትንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ አስረዱ፤ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ተጉዘውም በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ መጡ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወደነበሩት ወደ ሙሴና አሮን ወደ መላውም የእስራኤል ማኅበር መጡ፤ እነርሱም ያዩትን ነገር ሁሉ አስረዱ፤ ያመጡትንም ፍሬ አሳዩአቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በፋራን ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 13:26
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ተመ​ል​ሰ​ውም ቃዴስ ወደ ተባ​ለች ወደ ፍርድ ምንጭ መጡ፤ የአ​ማ​ሌ​ቅን አለ​ቆች ሁሉና በአ​ሳ​ሶን ታማር የሚ​ኖሩ አሞ​ራ​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።


አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ወደ አም​ላ​ኬም ለመ​ንሁ።


ምድ​ሪ​ቱ​ንም ሰል​ለው ከአ​ርባ ቀን በኋላ ከዚያ ተመ​ለሱ።


ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከፋ​ራን ምድረ በዳ ላካ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ነበሩ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ወደ ጺን ምድረ በዳ መጡ፤ ሕዝ​ቡም በቃ​ዴስ ተቀ​መጡ፤ ማር​ያ​ምም በዚያ ሞተች፤ ተቀ​በ​ረ​ችም።


ሙሴም ከቃ​ዴስ ወደ ኤዶ​ም​ያስ ንጉሥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን እን​ዲህ ብሎ ላከ፥ “ወን​ድ​ምህ እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይላል፦ ያገ​ኘ​ንን መከራ ሁሉ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድም​ፃ​ች​ንን ሰማ፤ መል​አ​ክ​ንም ልኮ ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤ እነ​ሆም፥ በም​ድ​ርህ ዳርቻ ባለ​ችው ከተማ በቃ​ዴስ ተቀ​ም​ጠ​ናል።


ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ክ​ኋ​ቸው ጊዜ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን?


ወደ ወይን ዘለላ ሸለቆ መጡ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም አዩ​አት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሰጣ​ቸው ምድር እን​ዳ​ይ​ገቡ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ልብ መለሱ።


ከጋ​ስ​ዮ​ን​ጋ​ቤ​ርም ተጕ​ዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ከጺን ምድረ በዳም ተጕ​ዘው በፋ​ራን ምድረ በዳ ሰፈሩ። ይህ​ችም ቃዴስ ናት።


“ከኮ​ሬ​ብም ተጓ​ዝን፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በታ​ላቁ፥ እጅ​ግም በሚ​ያ​ስ​ፈራ በዚያ ባያ​ች​ሁት ምድረ በዳ ሁሉ በኩል በአ​ሞ​ሬ​ዎን ተራራ መን​ገድ ሄድን፤ ወደ ቃዴስ በር​ኔም መጣን።


በሴ​ይር ተራራ መን​ገድ ከኮ​ሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የዐ​ሥራ አንድ ቀን ጕዞ ነው።


የይ​ሁ​ዳም ልጆች በጌ​ል​ገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔ​ዛ​ዊ​ውም የዮ​ፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአ​ም​ላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቃ​ዴስ በርኔ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ታው​ቃ​ለህ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ምድ​ርን እሰ​ልል ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ከኝ ጊዜ እኔ የአ​ርባ ዓመት ሰው ነበ​ርሁ፤ እኔም በልቡ የነ​በ​ረ​ውን ቃል መለ​ስ​ሁ​ለት።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች