የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 32:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኛስ በአ​ንተ ዘንድ ሞገ​ስን አግ​ኝ​ተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ርስት አድ​ር​ገህ ስጠን፤ ዮር​ዳ​ኖ​ስን አታ​ሻ​ግ​ረን።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በፊትህ ሞገስ ያገኘን ከሆነ ይህ ምድር ለእኛ ለአገልጋዮችህ በርስትነት ይሰጠን፤ ዮርዳኖስንም እንድንሻገር አታድርገን።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም በመቀጠል እንዲህ አሉ፦ “እኛስ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝተን እንደሆነ ይህን ምድር ለባርያዎችህ ርስት አድርገህ ስጠን፤ ወደ ዮርዳኖስም ማዶ አታሻግረን።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ንግግራቸውንም በመቀጠል፦ “በፊታችሁ ሞገስን አግኝተን ከሆነ ይህን ምድር ለእኛ ለአገልጋዮቻችሁ በርስትነት እንዲሰጠን አድርጉ እንጂ ዮርዳኖስን እንድንሻገር አታድርጉ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኛስ በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝተን እንደ ሆነ ይህን ምድር ለባሪያዎችህ ርስት አድርገህ ስጠን፤ ወደ ዮርዳኖስም ማዶ አታሻግረን።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 32:5
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ ባሪ​ያህ በፊ​ትህ ምሕ​ረ​ትን አግ​ኝቼ እን​ደ​ሆነ፥ ሰው​ነ​ቴ​ንም ታድ​ናት ዘንድ፥ ቸር​ነ​ት​ህን አብ​ዝ​ተ​ህ​ልኝ እንደ ሆነ፥ መከራ አግ​ኝ​ቶኝ እን​ዳ​ል​ጠፋ ወደ ተራራ ሸሽቼ ራሴን ማዳን አል​ች​ልም።


ኢዮ​አ​ብም በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ ሰገ​ደ​ለት፤ ንጉ​ሡ​ንም አመ​ሰ​ገነ፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ነገር አድ​ር​ገ​ሃ​ልና በዐ​ይ​ንህ ፊት ሞገ​ስን እን​ዳ​ገኘ አገ​ል​ጋ​ይህ ዛሬ ዐወቀ” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከሰ​ይፍ የተ​ረ​ፈው ሕዝብ በም​ድረ በዳ ሞገስ አገኘ። ሂዱ፦ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አታ​ጥፉ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የሰ​ጣት ምድር የከ​ብት መሰ​ማ​ሪያ ሀገር ናት፤ ለእ​ኛም ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ብዙ እን​ስ​ሳት አሉን።


ሙሴም ለሮ​ቤል ልጆ​ችና ለጋድ ልጆች አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ወደ ጦር​ነት ሲሄዱ እና​ንተ በዚህ ትቀ​መ​ጣ​ላ​ች​ሁን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በእኔ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደ​ዚያ አት​ገ​ባም፤


ኢያ​ሱም አለ፥ “ወዮ! ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን እጅ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጠን፥ ታጠ​ፋ​ንም ዘንድ አገ​ል​ጋ​ይህ ይህን ሕዝብ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ለምን አሻ​ገረ? በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ተቀ​ም​ጠን በኖ​ርን ነበር እኮ!


በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው።


ዳዊ​ትም፥ “እኔ በፊ​ትህ ሞገ​ስን እን​ዳ​ገ​ኘሁ አባ​ትህ በእ​ው​ነት ያው​ቃል፤ እር​ሱም፦ ዮና​ታን እን​ዳ​ይ​ቃ​ወም አይ​ወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በሕ​ያው ነፍ​ስ​ህም እም​ላ​ለሁ፤ እኔ እን​ዳ​ል​ሁት በእ​ኔና በሞት መካ​ከል አንድ ርምጃ ያህል ቀር​ቶ​አል” ብሎ ማለ።