የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በአ​ዜብ በኩል ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የአ​ራድ ንጉሥ በአ​ታ​ሪን መን​ገድ እስ​ራ​ኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ሰልፍ አደ​ረገ ከእ​ነ​ር​ሱም ምርኮ ማረከ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ እስራኤል በአታሪም መንገድ መምጣቱን በሰማ ጊዜ በእስራኤላውያን ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል መምጣቱን ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ጦርነት አደረገ ከእርሱም ምርኮ ማረከ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መኖሪያው ኔጌብ የነበረ የከነዓናውያን ንጉሥ ዐራድ እስራኤላውያን በአታሪም በኩል መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በእነርሱ ላይ አደጋ ጥሎ ጥቂቶቹን ማረከ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በደቡብም በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ በአታሪም መንገድ እስራኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእስራኤልም ጋር ሰልፍ አደረገ ከእነርሱም ምርኮ ማረከ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 21:1
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ራ​ምም ከዚያ ተነሣ፤ እየ​ተ​ጓ​ዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚ​ያም ኖረ።


በዚ​ያም ተራራ ላይ የተ​ቀ​መጡ ዐማ​ሌ​ቃ​ዊና ከነ​ዓ​ናዊ ወረዱ፤ መት​ተ​ዋ​ቸ​ውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው። ወደ ከተ​ማም ተመ​ለሱ።


በከ​ነ​ዓን ምድ​ርም ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የዓ​ራድ ንጉሥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ።


ሴዎ​ንም ሕዝ​ቡም ሁሉ ሊዋ​ጉን ወደ ኢያሳ ወጡ።


የኤ​ር​ሞት ንጉሥ፥ የዓ​ራድ ንጉሥ፥


የጋይ ሰዎ​ችም ከእ​ነ​ርሱ ሠላሳ ስድ​ስት ሰዎ​ችን ገደሉ፤ ከበሩ ጀም​ረው እስከ አጠ​ፉ​አ​ቸው ድረስ አባ​ረ​ሩ​አ​ቸው፤ በቍ​ል​ቍ​ለ​ቱም ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ የሕ​ዝ​ቡም ልብ ደነ​ገጠ፤ እንደ ውኃም ሆነ።


የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ።