የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 19:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ስ​ዋ​ንም ለካ​ህኑ ለአ​ል​ዓ​ዛር ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዷ​ታል፤ በፊ​ቱም ያር​ዷ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለካህኑ ለአልዓዛርም ስጠው፤ ከሰፈሩ አውጥተውም በፊቱ ይረዷት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሷንም ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጣላችሁ፥ እርሷም ከሰፈር ወደ ውጭ ትወሰዳለች፥ እርሷም በእርሱ ፊት ትታረዳለች።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጊደርዋንም ለካህኑ ለአልዓዛር ስጡት፤ ከሰፈርም ወጥታ በእርሱ ፊት ትታረድ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርስዋንም ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጣላችሁ፥ እርስዋንም ከሰፈር ወደ ውጭ ይወስዳታል፥ አንድ ሰውም በፊቱ ያርዳታል።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 19:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያም እን​ዲ​ሆን ደማ​ቸው ወደ መቅ​ደስ የገ​ባ​ውን የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ንና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ያወ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ ቍር​በ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ ሥጋ​ቸ​ው​ንም፥ ፈር​ሳ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ።


“ተሳ​ዳ​ቢ​ውን ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አው​ጣው፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን በራሱ ላይ ይጫ​ኑ​በት፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።”


የወ​ይ​ፈ​ኑን ቍር​በት፥ ሥጋ​ው​ንም ሁሉ፥ ራሱ​ንም፥ እግ​ሮ​ቹ​ንም፥ ሆድ ዕቃ​ው​ንም፥ ፈር​ሱ​ንም፤


ወይ​ፈ​ኑን ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አመድ ወደ​ሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ አመድ በሚ​ፈ​ስ​ስ​በት ስፍራ ይቃ​ጠ​ላል።


ወይ​ፈ​ኑ​ንም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም ወይ​ፈን እን​ዳ​ቃ​ጠሉ ያቃ​ጥ​ሉ​ታል፤ የማ​ኅ​በሩ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና።


ማኅ​በ​ሩም ሁሉ ከሰ​ፈሩ ወደ ውጭ አወ​ጡት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት።


ንጹ​ሕም ሰው የጊ​ደ​ሪ​ቱን አመድ ያከ​ማ​ቻል፤ ከሰ​ፈ​ሩም ውጭ በን​ጹሕ ስፍራ ያኖ​ረ​ዋል፤ ርኵ​ሰት ለሚ​ያ​ነጻ ውኃ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ይጠ​በ​ቃል፤ ይነ​ጹ​በ​ታ​ልና።


ናዳ​ብና አብ​ዩድ በሲና ምድረ በዳ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሌላ እሳት ጭረው አም​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ቸ​ውም። አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ምር ከአ​ባ​ታ​ቸው ከአ​ሮን ጋር በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ነበር።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለም​ጻ​ሙን ሁሉ ፈሳሽ ነገ​ርም ያለ​በ​ትን ሁሉ በሰ​ው​ነቱ የረ​ከ​ሰ​ውን ሁሉ ከሰ​ፈሩ እን​ዲ​ያ​ወጡ እዘ​ዛ​ቸው፤