የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘኍል 13:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከፋ​ራን ምድረ በዳ ላካ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ​ቆች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሙሴ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ እነዚህን ላካቸው፤ ሁሉም የእስራኤላውያን አለቆች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም እንደ ጌታ ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ መሠረት ከእስራኤል መሪዎች መካከል ከፋራን ምድረ በዳ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘኍል 13:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየ​ጉ​ዞ​አ​ቸው ተጓዙ፤ ደመ​ና​ውም በፋ​ራን ምድረ በዳ ቆመ።


ከዚ​ያም በኋላ ሕዝቡ ከአ​ሴ​ሮት ተጓዙ፤ በፋ​ራ​ንም ምድረ በዳ ሰፈሩ።


“ይገ​ዙ​አት ዘንድ እኔ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የም​ሰ​ጣ​ትን የከ​ነ​ዓ​ንን ምድር የሚ​ሰ​ልሉ ሰዎ​ችን ላክ፤ ከአ​ባ​ቶች ቤት ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነገድ ሁሉ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አለቃ የሆነ አንድ አንድ ሰው ትል​ካ​ላ​ችሁ።”


ገሥ​ግ​ሠ​ውም በቃ​ዴስ ፋራን ምድረ በዳ ወዳ​ሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ደረሱ፤ ወሬ​ው​ንም ለእ​ነ​ር​ሱና ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው፤ የም​ድ​ሪ​ቱ​ንም ፍሬ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


ስማ​ቸ​ውም ይህ ነበረ፤ ከሮ​ቤል ነገድ የዝ​ኩር ልጅ ሰሙ​ኤል፤


ምድ​ሪ​ቱን ይሰ​ልሉ ዘንድ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ክ​ኋ​ቸው ጊዜ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ እን​ዲህ አድ​ር​ገው አል​ነ​በ​ረ​ምን?


“ምድ​ሪ​ቱን ርስት አድ​ር​ገው የሚ​ከ​ፍ​ሉ​ላ​ችሁ ሰዎች ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አል​ዓ​ዛ​ርና የነዌ ልጅ ኢያሱ።


“ከኮ​ሬ​ብም ተጓ​ዝን፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በታ​ላቁ፥ እጅ​ግም በሚ​ያ​ስ​ፈራ በዚያ ባያ​ች​ሁት ምድረ በዳ ሁሉ በኩል በአ​ሞ​ሬ​ዎን ተራራ መን​ገድ ሄድን፤ ወደ ቃዴስ በር​ኔም መጣን።


ያም ነገር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ከእ​ና​ን​ተም ዐሥራ ሁለት ሰው ወሰ​ድሁ፤ ከየ​ነ​ገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ውጡ፤ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁ​ንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃ​ዴስ በርኔ በላ​ካ​ችሁ ጊዜ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ዐመ​ፃ​ችሁ፤ በእ​ር​ሱም አላ​መ​ና​ች​ሁም፤ ቃሉ​ንም አል​ሰ​ማ​ች​ሁም።


ሳሙ​ኤ​ልም ሞተ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በው አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ በአ​ር​ማ​ቴ​ምም በቤቱ ቀበ​ሩት። ዳዊ​ትም ተነ​ሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ።