እግዚአብሔር ወዳለውም ወደዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያዉን ሠራ፤ ዕንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያዉ በዕንጨቱ ላይ በልቡ አስተኛው።
ማቴዎስ 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካሰሩትም በኋላ ወስደው ለገዢው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱና ለገዥው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስረውም ወሰዱት፥ ለገዢው ለጴንጤናዊው ጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት። |
እግዚአብሔር ወዳለውም ወደዚያ ቦታ ደረሱ፤ አብርሃምም በዚያ መሠዊያዉን ሠራ፤ ዕንጨትንም ረበረበ፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያዉ በዕንጨቱ ላይ በልቡ አስተኛው።
ከእነርሱም ተለይተው ከሄዱ በኋላ፥ የሚጠባበቁትን አዘጋጁለት፤ በአነጋገሩም ያስቱት ዘንድ ወደ መኳንንትና ወደ መሳፍንት አሳልፈው ሊሰጡት ራሳቸውን የሚያመጻድቁ ሰላዮችን ወደ እርሱ ላኩ።
ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በዐሥራ አምስት ዓመት ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ገዢ ሆኖ ሳለ፥ ሄሮድስም በገሊላ የአራተኛው ክፍል ገዢ ሳለ፥ ወንድሙ ፊልጶስም የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አራተኛ ክፍል ገዢ፥ ሊሳንዮስም የሳብላኒስ አራተኛ ክፍል ገዢ ሆነው ሳሉ፥
ጌታችን ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ፍርድ አደባባይ ወሰዱት፤ አይሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋሲካውን በግ ሳይበሉ እንዳይረክሱ ወደ ፍርድ አደባባይ አልገቡም።
ሄሮድስም ማለዳ ያቀርበው ዘንድ በወደደባት በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ ሁለቱን እጆቹን በሰንሰለት ታስሮ በሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም የወኅኒ ቤቱን በር ይጠብቁ ነበር።
ሊገርፉትም በአጋደሙት ጊዜ ጳውሎስ በአጠገቡ የነበረውን የመቶ አለቃ፥ “የሮማን ሰው ያለ ፍርድ ልትገርፉ ይገባችኋልን?” አለው።
ሁለት ዓመትም ካለፈ በኋላ፥ ፊልክስ ተሻረና ጶርቅዮስ ፊስጦስ የሚባል ሌላ ሀገረ ገዢ በእርሱ ቦታ መጣ፤ ፊልክስም በግልጥ ለአይሁድ ሊያዳላ ወደደ፤ ስለዚህም ጳውሎስን እንደ ታሰረ ተወው።
ስለዚህም ላያችሁ፥ ልነግራችሁና ላስረዳችሁ ወደ እኔ እንድትመጡ ማለድኋችሁ፤ ስለ እስራኤል ተስፋ በዚህ ሰንሰለት ታስሬአለሁና።”
የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ፥ የአባቶቻችንም አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትን፥ እርሱም ሊተወው ወዶ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ልጁን ኢየሱስን ገለጠው።
በቀባኸው በቅዱስ ልጅህ ላይ ሄሮድስና ጰንጤናዊው ጲላጦስ ከወገኖቻቸውና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በእውነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ።
ምንአልባት በመንገድ የሚያገኘው ሰው ቢኖር ወንዶችንም ሴቶችንም እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች የሥልጣን ደብዳቤ ከሊቀ ካህናቱ ለመነ።
ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ።
እነርሱም፥ “አስረን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፈን ልንሰጥህ መጥተናል” አሉት። ሶምሶንም፥ “እናንተ እንዳትገድሉኝ ማሉልኝ፤ ለእነርሱም አሳልፋችሁ ስጡኝ፤ እናንተ ግን ከእኔ ጋር አትዋጉ” አላቸው።